ፈረሰኞቹ በ አራቱ ተጫዋቾቹ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላለፉ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከሳምንታት በፊት በ ክለቡ አራት ተጫዋቾች ላይ ጌታነህ ከበደ ፣ ጋዲሳ መብራቴ ፣ አስቻለው ታመነ እና ሙሉአለም መስፍን ባሳዩት ” ተደጋጋሚ ” የዲሲፕሊን ጥሰት ማገዳቸው የሚታወስ ነው ።

ይህንንም ተከትሎ ተጫዋቾቹ ቡድኑ ካለበት ሳምራ ሆቴል ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው የሚታወስ ነው ።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ከ ደቂቃዎች በፊት በ ክለቡ የራዲዮ ፕሮግራም ምንጊዜም ጊዮርጊስ ላይ እንዳሳወቁት አራቱም ተጫዋቾች እያንዳንዳቸው 20 ሺ ብር እና ውላቸው እስኪያልቅ ድረስ ከቡድኑ ጋር እንዳይቀላቀሉ መታገዳቸው ተነግሯል ።

የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀል እንዳሳወቁት ከሆነ ተጫዋቾቹ የተለያዩ የምስል እና የ ቪድዮ ማስረጃዎች እንደተገኙባቸው እና የክለቡ ደጋፊዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ትብብረን ማድረጋቸውን በመግለፅ ምስጋናቸውን ለደጋፊዎቹ አስተላልፈዋል ።

የክለቡ ከፍተኛ ሀላፊዎች ከሀትሪክ ስፖርት ጋር ከቀናት በፊት ቆይታን ማድረግ ሲችሉ በወቅታዊ የክለባቸው ጉዳዮች ላይ የሚከተለውን አስተያየቶች ማንሳታቸው የሚታወስ ነው ።

• ” ቡድናችንን ሀትሪክ ሰርቶ ውጤታማ የሚያደርግ ተጨዋች እንጂ በዲሲፕሊን ግድፈት ሀትሪክ ለሚሰሩ ተጨዋቾች ቦታ የለውም ”

• ” ጌታነህም ቢሆን እንደ አምበል መሪነቱን አልተጠቀመበትም ”

• ” ሶስቱ ላይ በጅማ፣ በባህር ዳርና በድሬዳዋ የማያወላዳ ማስረጃ የቪዲዮ ሳይቀር ይዘናል ” ሲሉ አስተያየታቸውን መስጠታቸው የሚታወስ ነው ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የድሬደዋ ቆይታውን በሽንፈት ሲያገባድድ በቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ 9:00 ሰዓት በሀዋሳ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor