ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

*……የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ ከዋሊያዎቹ ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸው ተረጋግጧል… ከ8 አመት በኋላ የማለፍ ገድል የከሰተው አሰልጣኝ ውበቱ ” የህዝቡ ደስታ አኩርቶኛል.. ከእንኳን አደረሰህ መልእክቶች መሃል የአዛውንቶችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ደስታ በልቤ ትልቅ ትርጉም አለው” ብሏል።

*…የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ “የተገኘው ድል ለህዝቡ ለአፍሪካ ዋንጫ ከማለፍም በላይ ትርጉም ያለው ነው” ሲሉ ለዋሊያዎቹ ሙገሳ ቸረዋል

*…የዋሊያዎቹ ምክትል አሰልጣኝ አስራት አባተ በበኩሉ “ከፍ ለማይል እግርኳስ የሚለውን መጥፎ አባባል ለማሰረዝ እድሉን አግኝተናል” ሲል ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፋችንን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ገልጿል።

*….የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ “የውጤት ድምሩ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ቢያሳልፈንም ትልቁን ምስጋና ማግኘት ያለበት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ነው” በማለት ክብር ለሚገባው ክብር የሰጠበትን ቃለምልልስ ከሀትሪክ ጋር አድርጓል”

*….ከ31 አመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ በታላቅ ገድል የመለሱን ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው” የሰውነት ሪከርድ ተሰበረ ሲባል እሰማለሁ እኔ የ10ሺ ሜትር ራጭ ነኝ እንዴ?” በማለት የግርምት አስተያየት የሰጡበት ጠንካራ ቃለ ምልልስ ከሀትሪክ ጋርአድርገዋል።

*….የአቢጃኗ የ9 ደቂቃ አስገራሚ ገጠመኝ ሀዘንና ደስታ የተፈራረቀበት 2 ግብ ካገቡ በነፍስ ወከፍ ሊሰጣቸው የተገባላቸውን የ50ሺህ ብር ሽልማት ግብ አግቢ ባለመገኘቱ ሳይሰጣቸው ስለቀሩበት አስገራሚ ክስተት በሀትሪክ ተዳሷል።

ከውጪ ዘገባዎቻችን:-

*…. አጓጊው የሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ማክሰኞና ረቡእ ይቀጥላል በጨዋታዎቹ ዙሪያ መረጃዎችን ይዘናል….

*….የሊቨርፑሉ ኮከብ ተጨዋች ሞ ሳላህ….ከሪያል ማድሪድ ጋር ሲገናኙ ራሞስን ለመበቀል እንደማያስብ በመግለጽ ህሊናው ውስጥ በቀል ቦታ እንደሌለው የገለጸበት ምርጥ ቃለምልልስ ተካቷል።

*….የአለማችን ውጤታማ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ቻፕማን ፈርጉሰን ከረጅም አመታት ቆይታ በኋላ ስለ አሰልጣኝነት ህይወታቸው የተነፈሱበትን ቃለምልልስ ይዘናል።

*….በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነገ ምሽት 4 ሰአት የኢምሬትስ የአርሰናልና የሊቨርፑል ጠንካራ ጨዋታ ዙሪያ ላይ የሚያጠነጥን ዘገባም ይዘናል።

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

https://www.hatricksport.net

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team