መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

አጋራ
አጋራ

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ  ሃላፊነቱን ከተረከቡ ድፍን አንድ  አመት  ሞልቷቸዋል። በሀገር ውስጥ ዘገባችን  ዛሬ 10 ሰአት ላይ ከባፋና ባፋና ደቡብ አፍሪካ ጋር   ወሳኙን ጨዋታ የሚያደርጉት የዋሊያዎቹ አለቃ ውበቱ አባተ እንግዳችን  ነው…. አሰልጣኙ ከይስሃቅ በላይ ጋር  በነበራቸው ቆይታ  እንደተናገሩት”አሁን እየተጫወተ ያለ አልመረጥኩትም ብዬ የምጸጸትበት አንድም ተጨዋች በሀገር ውስጥ የለም”ሲሉ የተናገሩ ሲሆን “እኔ ቂመኛ አይደለሁም በሀሳቡ ምክንያት የምጠላው ተጨዋችም የለም” ሲሉም ጠንካራ አስተያየት ሰጥተዋል።

*….በሲቲ ካፑ  ፍጻሜ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማሳካት መከላከያና  ባህርዳር ተፋጠዋል…ከሀትሪኩ መሸሻ ወልዴ  ጋር ቆይታ ያደረገው የመከላከያው ቢኒያም በላይ
“አሸናፊ ቡድን አለን የሲቲ ካፑንም ዋንጫ እናነሳለን”ሲል ፎክሯል… ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ያወጋው ተስፈኛው ግብ ጠባቂ “አቡበከር ኑራ ..” አልተሳሳትኩም ግብ ጠባቂው የአባቴ ስም ኑሪ አይደለም ኑራ ነው ይስተካከል ብሏል” በሲቲ ካፑ የመጀመሪያው ዋንጫ ያነሳ የክልል ክለብ እንሆናለን” ሲል የባህርዳሩ ግብ ጠባቂ ተናግሯል። አቡበከር “ለባህርዳር ከተማ  የፈረምኩት አሰልጣኝ አብርሃም ከአሰልጣኝ ውበቱ ዋሊያዎቹ አጨዋወት ጋር ስለሚቀራረብ ዋሊያዎቹን እንደምቀላቀል  ተስፋ አድርጌ ነው ” ብሏል።

*….. ከሲቲ ካፑ አልወጣንም….. የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ም/ል ፕሬዝዳንትና የማርኬቲንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደረጄ አረጋ ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበራቸው ቆይታ “ለቀረበልን ሀገራዊ ጥሪ በጎ ምላሽ ለመሰጠት እንጂ ገንዘብ  ለመለመን ወደ ባህርዳር አልተጓዝንም” ሲሉ ገንዘብ ለመለመን ወደ ባህርዳር ተጓዙ የሚለውን ሃሳብ ተችተዋል።

*…ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በ8 ማለቂያ በአራት ቅይይር የተባለ ይመስል ሩዋንዳን በሀገሯ 4ለ0  ረትተው ከተመለሱ በኋላ በባህርዳር የመልስ ጨዋታ በተመሳሳይ 4 ለ 0 በአጠቃላይ 8 ለ 0  በመርታት ወደ ቀጣዪ ዙር አልፈዋል…. ከመሸሻ ወልዴ ጋር  ቆይታ ያደረገችው አምበሏ ናርዶስ  ጌትነት ” ለኮስታሪካው የአለም ዋንጫ ለማለፍ አቅደናል” በማለት ህልማቸውን አጋርተዋለች።

በውጪው ዘገባዎቻችን ደግሞ…

*…. ኮከቡ አርጀንቲናዊ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ  ከልጅነት ክለቡ ባርሴሎና  ወደ ፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ፒ ኤስ ጂ  ማቅናቱ ይታወቃል… በፈረንሳዩ ክለብ  የተጀመረውን  የሊዮኔል ሜሲን አዲስ ህይወት የሚመለከት ዘገባ አካተናል….

 *….. አንድ ጥያቄ እናቅርብልዎ….የአርሰናል ወጣት ተስፈኞችን እስቲ ይግለጹልን ?…..በእኛ በኩል የመድፈኞቹን የወደፊቱ አምስት ተስፈኛ ተጨዋቾችን በተመለከተ መረጃዎችን አካተናል…

*…..ማርቲን ኦዲጋርድ በአርሰናል ቋሚ ኮንትራት ከመፈረሙ በፊት የሪያል ማድሪድ ተጨዋች  መሆኑ  ይታወቃል….ተጨዋቹ .የሳንቲያጎ በርናባው ቆይታው ፈታኝ እንደነበር የገለጸበትን ቃለምልልስ ይዘናል…

*…. ከሰሞኑ የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ስለ ሞ.ሳላህ አድናቆታቸውን እያዘነቡለት ነው ግብጻዊው በልዩ ብቃት ላይ ይገኛል እኛም የግብጻዊው ኢንተርናሽናል የማይዘነጉ የሊቨርፑል ጎሎችን አዘጋጅተናል

 *…. የስፔኑ ሃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ውጤታማ አልሆነም
 ብዙዎቹ ክለቡ  ምን ነካው..? እያሉ ነው  ጣሊያናዊው
  አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከወዲሁ ጫና ውስጥ
  ገብተዋል…መረጃዎችን ይዘናል

*…. የማን.ዩናይትዱ ዲያን ሄንደርሰን ይናገራል….”
“በዩናይትድ መለያ ምርጡ ብቃቴን ገና አላየሁም”ሲልም
 ወደፊት ብሩህ ጊዜ እንዳለው ይናገራል…..

*…… ዑራጓዊው  ኮከብ ኤዲሰን ካቫኒ  የኦልድትራፎርድ ቆይታው አመት ሞልቶታል… እኛም የአጥቂውን የአንድ  አመት የዩናይትድ ቆይታን ዳሰነዋል….

……እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት  አዳዲስ መረጃዎችን   የሚያገኙበት  ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
        የተባረከ ይሁን……

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...