ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን የሀትሪኩ ኮከብ ቡናማው አቡበከር ናስር እንግዳችን ነው….ከይስሀቅ በላይ ጋር በነበረው ሰፊ ቆይታ ምርጥ ቃለምልልስ አድርጓል…ስለቤተሰቦቹ ተናግሮ የማይጠግበው አቡኪ “ቤተሰቦቼ ልጃቸውን በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት እንደዳሩ ተሠምቷቸዋል በነሱም ደስታ ተደስቻለሁ አንገታቸውን ቀና አድርገው በመሄዳቸውም ትልቅ ርካታ ተሠምቶኛል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል…

*….ደመወዝ ተከልክሎም ቢሆን በከፍተኛ የራስ መተማመን ኮከብ መሆን እንደሚቻል ያሳየው የሀዋሳ ከተማና የኢትዮጵያ እግርኳስ ተስፈኛ ወንድማገኝ ሃይሉ “ባልተከፈለኝ ደመወዝ ከማዘን ይልቅ ባገኘሁት የመጫወት ዕድል መደሰትህን መርጫለሁ” ሲል የሀዋሳው ዝላታን ኢብራሂሞቪች ተናግሯል።

*….ፈረሰኞቹ ላለፉት አራት አመታት ባልተለመደ መልኩ ዋንጫ አላገኙም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ዋንጫ ካላገኙት ተጨዋቾች መሃል አንዱ የሆነው አብዱልከሪም መሃመድ ደግሞ “ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት አመት ዋንጫ ያጣው በኛ ጊዜ መሆኑ ለታሪክ ተወቃሽነት ዳርጎናል” ሲል ተርሚኔተሩ ተናግሯል….

*…. ፋሲል ከነማ አመቱን በድል ጨርሷል… አሁን ደግሞ ወደ ሌላ አጀንዳ ፊቱን አዞሯል…”ጠንካራ ነን በቀጣዮቹ 10 አመታት የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮን የመሆን እቅዱ አለን” ሲል የክለቡ ተጨዋች ሰይድ ሁሴን አስተያየቱን ሰጥቷል…..

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*….. በፖርቱጋሉ ኮከብ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ስኬታማ የማን.ዩናይትድ ቆይታ ዙሪያ ያዘጋጀነው ዘገባ አለ….

*…. ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶሻንቶሽ አቪየሮ ስለ አስደናቂው የእግር ኳስ ህይወቱ ያወጋናል…

*….ከማን.ሲቲ ጋር ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈውና ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት በኑካምፕ ከሀገሩ ልጅ ሜሲ ጋር ለመጫወት ወደ ካታላን ምድር ያቀናው ኩን አጉየሮ “ባርሴሎና የአለማችን ምርጡ ክለብ ነው” ሲል አዲሱ ክለቡን አሞግሷል….

*…. የሊቨርፑሉ አንዲ ሮበርትሰን “ሀገሬን በአምበልነት መምራት በመቻሌ አኩርቶኛል”ሲል የስኮትላንድ አምበል መሆን የሚፈጥረውን ደስታ ተናግሯል…

*…..የቀድሞ የአርሰናል የአሁኑ የጁቬንቱስ የመሃል ሜዳ ታጋይ አሮን ራምሴ ስለ ሀገሩ ዌልስ የ2016 ገድል ይናገራል…

*… የማን.ሲቲው ኮከብ ራሂም ስተርሊንግ በሶስቱ አናብስት ካምፕ ውስጥ ይገኛል…. ስለ የአውሮፓ ዋንጫ የተናገረው ተጨዋቹ “በአውሮፓ ዋንጫው ለእንግሊዝ ከሻምፒዮናነት ያነሰ ውጤት ተቀባይነት የለውም” ሲል ዋንጫን እንጂ ሌላ አላማ ይዘው መጓዝ እንደሌለባቸው ፎክሯል…

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team