ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን የአዲሶቹ ሻምፒዮኖች አጼዎቹ ኮከብ በዛብህ መለዮ እንግዳችን ነው ….
“የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት ህልሜ ከፋሲል ጋር በመሳካቱ አሁን ኳስ ባቆም ቅር አይለኝም” ሲል ደስታውን አጋርቷል…. “ልጄን በጸሎት ያልኳት በጸሎት የተገኘች ልጅ ስለሆነችነው” ሲልም ያመሰግናል….ስለሚስቱ ስለክለቡ ደጋፊዎች ተናግሮ አያበቃም….

2ኛ ሆኖ በኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮዽያን ማን ይወክላል? ተፋላሚዎቹን አነጋግረናል

“በኮንፌዴሬሽን ካፕ የማለፍ እድሉ አሁንም በእጃችን ላይ ነው ያለው..ህልማችንም ይሳካል” ሲል የኢትዮዽያ ቡናው ሀብታሙ ታደሰ ተናግሯል።
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ምንተስኖት አዳነ “ለቅዱስ ጊዮርጊስ ባይመጥንም በኮንፌዴሬሽን ካፕ ለመሳተፍ ብለን ጠንክረን እየሰራን ነው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። ምንተስኖት እንደሚያምነው በቀጣይ ከሀዲያ ሆሳዕና ታላቅ ፍልሚያ እንደሚጠብቃቸው የተናገረ ሲሆን ለዚህም “ከሳላህዲን ሰይድ ውጪ ሁሉም ተጨዋች እንደ ቻይናዊያን መልክ ተመሳሳይ ነው”ሲል እምነቱን ገልጿል።

የባህርዳር ከተማው ምንይሉ ወንድሙ “ተስፋ ባንቆርጥም ከቡና ጋር አቻ መለያየታችን የሌላ ቡድንን ውጤት እንድንጠብቅ አስገዶናል” ሲል የሀድያ ሆሳዕናው ሚካኤል ጆርጅ በበኩሉ”ለ2ኛነት ተስፋ ባንቆርጥም ከባድ ፍልሚያ ግን ይጠብቀናል ብዬ እሰጋለሁ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

*…ሀዋሳ ላይ ግብ ያስቆጠረው የአዳማው አብዲሳ ጀማል “ሀዋሳ ከተማ ላይ ግብ እንደማስቆጥር ለአሰልጣኙ አስቀድሜ ነግሬው ነበር” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

….በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*…….ውጤታማ መሆን ያቃተውና ከሁሉም የአውሮፓ ውድድር የተሰናበተው አርሰናል ቸልሲን ረቷል…
“ቸልሲን በረታው ቡድኔ ተደስቻለሁ”ብሏል ሚካኤል አርቴታ…

*….ከሊቨርፑል መራራ ሽንፈት እንማርበታለን” ብሏል የዩናይትዱ ኮከብ ብሩኖ ፈርናንዴዝ….

*…ስለ ሊቨርፑል ኮከብ ሞ ሳላህ
ከሊቨርፑል ጋር ስላደረጋቸው 200
ጨዋታዎች ዙሪያ የምንላችሁ አለ….

*…የዩናይትዱ የጎል ማሽን ኤዲሰን ካቫኒ
በቲያትር ኦፍ ድሪምስ ለመቆየት ለምን እንደወሰነ ይናገራል……

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……
https://www.Hatricksport.net

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team