ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ አርብ ግንቦት 6 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ።

1. ምንተስኖት ከበደ (ኢትዮጵያ ቡና) ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ 23 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ላይ በ48 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ይህንንም ተከትሎ ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት አንድ ጨዋታ እንዲታገድ ወስኗል።

2. እንዳለ ደባልቄ (ኢትዮጵያ ቡና) ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ 23 ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ላይ በ27 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት ሶስት ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።

3. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ 23 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ታፈሰ ሰለሞን ፣ ምንተስኖት ከበደ ፣ እንዳለ ደባልቄ ፣ ምንተስኖት ከበደ ፣ አበበ ጥላሁን ፣ አማኑኤል ዮሀንስ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል፡፡

4 አማኑኤል ዮሀንስ (ኢትዮጵያ ቡና) በአምስት ጨዋታዎች ላይ የቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ አንድ ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል።

5. ለአቶ ሰለሞን ታምራት (ኢትዮጵያ ቡና /የቦርድ አባል /) ሐሙስ ግንቦት 5 2013 ባህርዳር ከተማ – ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ 23 ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በውድድር አመራሮች ላይ የዛቻና የማስፈራራት ድርጊት መፈፀማቸው በውድድር አመራሮች ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ። በመሆኑም አቶ ሰለሞን ታምራት ለፈፀሙት ጥፋት ሶስት ወር ወደ ሜዳ እንዳይገቡ እንዲታገዱ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 4000 /አራት ሺህ/ እንዲከፍሉ ወስኗል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor