ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ቅሬታ ቀረበበት !

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በትላንትናው ዕለት በ ኤም ሲ አልጀርስ እና ዋይዳድ መካከል የተካሄደውን የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ መምራት ችለዋል ።

የአልጀርስ ክለብ ባለሜዳ በነበረበት በዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች አንድ አቻ በሆነ ውጤት መለያየት ችለዋል ።

የአልጀርሱ ክለብ በ 83ደቂቃ ላይ የአቻነቷን ግብ ሲያስቆጥሩ ቅሬታ ያቀረቡት ዋይዳዶች ” በጨዋታው ደካማ ዳኝነት ነበረ ” በማለት ለካፍ ቅሬታ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተገልጿል ።

ዋይዳዶች በጨዋታው መሪ የሆኑበትን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችለው ነበር ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor