ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን ስለ አዲሶቹ ሻምፒዮኖች አጼዎቹ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘናል….

አሰልጣኙ ስዩም ከበደ “የዋንጫው ድል መታሰቢያነት ለእናቴ ይሁንልኝ” ሲል የቡድን መሪው ሀብታሙ ዘዋለ “በ2011 ላጣነው ዋንጫ ትልቅ ካሳ ነው”ሲል ድሉን አሞካሽቷል።

*… “የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ማንሳት ህልሜ ነበር…ይህን ህልሜን ከፋሲል ከነማ ጋር በማሳካቴ የማላውቀው አይነት የደስታ ስሜት ተሰምቶኛል” ሲል የአጼዎቹ የመሃል ሜዳ ኮከብ ሱራፌል ዳኛቸው ተናግሯል።

*…. ” ሲዳማ ቡና በእኛ ዘመን አይወርድም…ማሊያውን ለብሶ እንደተጫወተ ኢትዮዽያ ቡና ስኬታማ በመሆኑ እደሰታለሁ እንጂ አልከፋም” ሲል የሲዳማ ቡናው አምበል ፈቱዲን ጀማል ተናግሯል…..

*… በቀጣይ ጨዋታዎች ኢትዮዽያ ቡናን ለአፍሪካ መድረክ ማብቃትና አቡበከር ናስር ኮከብ እንዲባል ለመርዳት ተዘጋጅተናል” ሲል ወጣቱ ኮከብ ዊሊያም ሰለሞን አስተያየቱን ሰጥቷል።

*…”ፋሲል ከነማን ለማሽነፍ ተዘጋጅተናል” ሲል የወልቂጤ ከተማው ፍሬው ሰለሞን / ጣቁሩ/ ዝቷል።

….በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*….. ስለማያረጀው የጎል ማሽን ኤዲሰን ካቫኒ ያዘጋጀነው ዘገባ አለ….

*…. የቸልሲው ሜሰን ማውንት
“ለታላቅ ክብር ተዘጋጅተናል” በማለት
አስተያየቱን ሰጥቷል።

*…. ” ስለ ሻምፒየንስ ሊጉ ግማሽ ፍጻሜ ንጉስ ሪያድ ማህሬዝም የምንላችሁ አለ……

*…..አርሰናል የዩሮፓ ሊግ የዋንጫ ተፋላሚ አለመሆኑን ተከትሎ የአሰልጣኙ ሚካኤል አርቴታ ቆይታ ላይ ጥያቄ ተነስቷል….

*….የሪያል ማድሪዱ ካሲሚሮ የቸልሲን ለፍጻሜ ማለፍ በጸጋ የተቀበለው ይመስላል…”ቸልሲ የተሻለው ቡድን በመሆኑ ለፍጻሜ መድረሱ ይገባዋል” ብሏል።

*…የማን.ዩናይትዱ አለቃ ኦሊጉናር ሶልሻየር” ለፍጻሜ በመድረሳችን አኩርቶኛል” ብሏል።

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……