የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ሊለወጥ ይሆን ?

የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ዙር ጨዋታዎች በ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ሲካሄድ ከስፍራው ባገኘነው መረጃ መሰረት የስታዲየም ለውጥ ሊደረግ እንደሚችል ታውቋል ።

የ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ወቅታዊውን ዝናባማ የአየር ሁኔታ አስመልክቶ አሸዋ እንደተደፋበት ለማወቅ ሲቻል ይህም ለጨዋታ አመቺ እንደማይሆን መታሰቡን ተከትሎ ለውጥ ሊደረግበት እንደሚችል ዛሬ ረፋድ በነበረ ውይይት ተገልጿል ።

ምን አልባትም ቀጣይ ጨዋታዎች በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የማይካሄዱ ከሆነ የሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም ቀጣይ ጨዋታዎች እንዲደረጉበት የተመረጠው ስታዲየም ሆኗል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor