መነሻ ገጽ ottawa marathon ሀትሪክ ለሶስተኛ ጊዜ የተጋበዘችበት የካናዳዊያን ታላቁ የማራቶን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል አበራ ኩማና ትርፌ ፀጋዬ ለአሸናፊነት ታጭተዋል
ottawa marathonሀትሪክ ስፖርት አትሌቲክስዜናዎች

ሀትሪክ ለሶስተኛ ጊዜ የተጋበዘችበት የካናዳዊያን ታላቁ የማራቶን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል አበራ ኩማና ትርፌ ፀጋዬ ለአሸናፊነት ታጭተዋል

አጋራ
አጋራ

በይስሀቅ በላይ ከካናዳ ኦቷዋ

 

ኤሌኖር ቶማስ የኦታዋን ማራቶን የአሸናፊነትን ክር በመበጠስ ያሸነፈች
የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ናት፡፡
ይህቺ አትሌት ከቀረቡት ሶስት እንስት
አትሌቶችና ተወዳዳሪዎች በላይ በውድድሩ
ነግሳ አዲስ ታሪክ ካፃፈች ድፍን 45 አመት
ሞልቷታል፡፡
ናሽናል ካፒታል ማራቶን በሚል
ስያሜ የተጀመረው የዛሬው የኦታዋ
ማራቶን የካናዳዊያን ብቻ ሳይሆን የሰሜን
አሜሪካ ኩራትና መመኪያም በመሆን
ላለፉት 45 አመታት ዘልቋል፡፡


ሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣ በኢትዮጵያ
የሚዲያ ታሪክ በተደጋጋሚ ማለትም
ለሶስተኛ ጊዜ ይሄንን የካናዳዊያንን ታላቅ
ውድድር በቦታው ተገኝታ በብቸኝነት
እንድትዘግብ የቀጥታ ግብዣ ተደርጎላት
የሀትሪክ ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ባለፈው ሳምንት
ወደ ውድድሩ ስፍራ ተጉዟል፡፡

በዓለማችን በቅዝቅዜ ከሚታወቁት
አገሮች በሰባተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው
የካናዳ የመንግሥት መቀመጫ የሆነችው
ኦታዋ የማራቶን ውድድሯን በ1975 ዓ.ም
በይፋ ስትጀምር 146 ተወዳዳሪዎች ብቻ
የተሳተፉ ሲሆን ይህ ቁጥር በከፍተኛ
ፍጥነት ተመንጥቆ ዛሬ የተወዳዳሪዎችን
ቁጥር ወደ 48 ሺህ አሳድጎታል፡፡ ከ14
በላይ ታላላቅ እና የቱሪስቶችን ቀልብ
የሚስቡ ሙዚየሞችን በውስጧ ሸሽጋ
የያዘችው ኦታዋ በ3 ሴትና በ146
አጠቃላይ ተወዳዳሪዎች የጀመረችው
የማራቶን ውድድር የIAAF የወርቅ ደረጃ
ያላቸውን ሁለት ውድድሮች ማለትም የ10
ኪሎ ሜትርና የማራቶን ውድድሮችን
በሁለት ቀን በማካሄድ የዓለማችን ብቸኛ
ከተማ አድርጎም ያስቀምጣታል፡፡
የመንግሥት መቀመጫና የሀገሪቱ ዋና
ከተማ ብቻ ሳይሆን የሩጫም ከተማ የሆነችው
ኦታዋ በየአመቱ የምታዘጋጀው የማራቶን
ውድድር የበርካቶችን ቀልብ በመሳብ ከሩጫ
ውድድርነት ባለፈ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ
የራሱን አስተዋፅኦ በማድረግ ከሩጫም በላይ
የሆነ አመታዊ ፌስቲቫል ሆኗል፡፡
እንደ ካናዳዊያና የኢኮኖሚ ተንታኞችና
የቱሪዝም ዘርፍ ባለሙያዎች አስተያየት ከሆነ
አመታዊው የኦታዋ ማራቶን በአገሪቱ ቀጥተኛ
ኢኮኖሚ (GDP) ላይ 14 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ
በማድረግ ከፊት ተሰልፏል፡፡ ከዚህም ባለፈ
በዕለቱ ከፍተኛ የሆነ የቻርቲ ስራ በመስራት
(ገንዘብ በማሰባሰብ) ማህበራዊ ኃላፊነቱን
በመወጣት ላይም ይገኛል፡፡ ባለፈው አመት
ከ69 በላይ የሆኑ ድርጅቶችም ተሳትፈው
በቻሪቲ ከ800 በመቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር
በላይ በማሰባሰብ ለበርካታ የእርዳታ ድርጅቶች
ፈሰስ በማድረግ በሰብዓዊነት ተግባር ላይ
በመሰማራትም ከበሬታን አግኝቷል፡፡ በIAAF
የወርቅ ደረጃ ያላቸው ሁለት ውድድሮች
የ10 ኪሎ ሜትርና የማራቶን ውድድሮችን
በሁለት ቀናት በማካሄድ የዓለማችን ብቸኛ
ውድድር ተደርጎ የተመዘገበው የኦታዋ
ማራቶን የፊታችን እሁድ በልዩ ድምቀት
ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አሁንም
እንደተለመደው በኤሊት አትሌቶች ፉክክር
ኢትዮጵያዊያን ከኬንያዊያንና ከኡጋንዳዊያን
አትሌቶች በተሻለ የአሸናፊነት ቅድመ
ግምት ከወዲሁ ተሰጥቷቸዋል፡፡


በ2018 በሮተርዳም ማራቶን 2፡05፡50
የግል ምርጥ ሰዓት ባለቤት የሆነው የ28
አመቱ ኢትዮጵያዊ አበራ ኩማ በወንዶች
አሸናፊነት ግምቱ ከፍ ያለ ሲሆን በሴቶች
ደግሞ ትርፌ ፀጋዬ በተመሳሳይ የአሸናፊነት
ሚዛኑን የምትደፋ አትሌት ናት በሚል
አይኖች ሁሉ በአሸናፊነት የሚጠብቃት
አትሌት ሆናለች፡፡
እንደ ውድድሮች አዘጋጆችና
የተለያዩ የዜና አውሮታሮች ዘገባ ከሆነ
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ በወንዶች
ኬንያዊው የ30 አመቱ ማርቲን ኮስጊ ሌላው
የአገሩ ልጅ የ26 አመቱ ማርዮስ ኩሙታይ
ኢትዮጵያዊው አያና ፀዳት እና የ39
አመቱ ካናዳዊው ሪይ ኩልሳት የሚጠበቁ
ሲሆን በሴቶች ደግሞ ኢትዮጵያኖቹ ሹካ
ገማኖ አበባ ተኮላ እና ትዕግስት ግርማ
የአሸናፊነት ሜዳሊያ ያጠልቃሉ ተብሎ
ከሚጠበቁ አትሌቶች በመጀመሪያው ረድፍ
ላይ ይገኛሉ፡፡
ከውድድሩ በፊት ለካናዳ ሚዲያዎች
አስተያየቷን የሰጠችው የ34 አመቷ
የቶኪዮ፣ የበርሊን፣ ለንደንና የቦስተን
ማራቶን ባለ ድል የሆነችው ትርፌ
በውድድሩ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓንና
የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደምትችል
ገልፃለች፡፡ ደራርቱ ቱሉ፣ ኃይሌ ገ/
ስላሴና ቀነኒሳ በቀለ ሲያሸንፉ ማየቷ
ለአትሌቲክስ ህይወቷ ከፍተኛ መነሳሳትን

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...