ሀዋሳ ከተማ የአዳማ አቻውን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡በጨዎታው የመጀመርያ ደቂቃዎች እንግዳዎቹ አዳማ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥሩ የተሻሉ ቢሆኑም ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ በመድረስ ጫና መፍጠር የቻሉት ሐዋሳ ከተማዎች በ11ኛው ደቂቃ መስፍን ታፈሰ ፍፁም ቅጣት ክልል ውስጥ ያገኘውን ወደ ግብ ቀይሮ ባለ ሜዳዎቹን መሪ አድጓቸዋል፡፡

ከግቧ መቆጠር በሗላ አዳማ ከተመዎች የሜዳ ብልጫ በመውሰድ ጫና ፈጥረው በመጫወት በ27ኛው ደቂቃ ፍ.ቅ.ም ክልል ጠርዝ ላይ የተገኘውን ቅጣት ምት ሙሀዚን ሙዲን በግሩም ሁኔታ ከመረብ አሳርፏት 1ለ1 ሆነዋል፡፡ወዲየው በመልሶ ማጥቃት ከአለሚን ከድር የተሻገረትን ኳስ ንጋቱ ሀይሉ ግብ ጠባቂውን አታሎ ወደ ግብ ቀይሯት ጨዋታው 2ለ1ሆኗል፡፡ 41ደቂቃ ሙሉቀን ከርቀት የመታት ኳስ የግቡን አናት መታ ወጣለች፡፡ የመጀመሪያ አጋማሽ በዚሁ ውጤት ተጠናቋል፡፡ በሁለተኛ አጋማሽ ሶስት ቅያሪ ዎች በማድረግ ወደ ሜዳ የገቡት ባለ ሜዳዎቹ ሐዋሳ ከተማዎች በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ግብ በመድረስ በ49ኛ ደቂቃ ላይ ወንደሰን ሐይሉ ከቅርብ ርቀት አስቆጥሯት ጫዎታው ሁለት አቻ አድርጎታል፡፡ የማህል ሜዳው ተቅጣጥሮ ኳስን መስርቶ በመጫዎቱ የተሻሉ የነበሩት አዳማ ከተማዎች ይህ ነው የሚባል ሙከራ ማድረግ አልቻሉም በአንፃሩ በጨዋታው የመጀመርያ ደቂቃዎች ጫና የፈጠሩት ሐዋሳ ከተማዎች በ88ተኛው ደቂቃ ሙሉቀን ታደሰ ወደ ግብ ቀይሯት ባለ ሜዳዎቹ ባለ ድል አድርጓቸዋል፡፡ጨዋታውም በሐዋሳ ከተማ 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
አስተያየት ይስጡ