መነሻ ገጽ U -17 ፕሪሚየር ሊግ ከ17 ዓመት በታች | የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ሐዋሳ ከተማ  የአዳማ አቻውን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
U -17 ፕሪሚየር ሊግሪፖርትዜናዎች

ከ17 ዓመት በታች | የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ሐዋሳ ከተማ  የአዳማ አቻውን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

አጋራ
አጋራ

ሀዋሳ ከተማ  የአዳማ አቻውን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡በጨዎታው የመጀመርያ ደቂቃዎች እንግዳዎቹ አዳማ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥሩ የተሻሉ ቢሆኑም ቶሎ ቶሎ  ወደ ግብ በመድረስ ጫና መፍጠር የቻሉት ሐዋሳ ከተማዎች በ11ኛው ደቂቃ መስፍን ታፈሰ ፍፁም ቅጣት  ክልል ውስጥ ያገኘውን ወደ ግብ ቀይሮ ባለ ሜዳዎቹን መሪ አድጓቸዋል፡፡

ከግቧ መቆጠር በሗላ አዳማ ከተመዎች የሜዳ ብልጫ በመውሰድ ጫና ፈጥረው በመጫወት በ27ኛው ደቂቃ ፍ.ቅ.ም ክልል ጠርዝ ላይ የተገኘውን ቅጣት ምት ሙሀዚን ሙዲን በግሩም ሁኔታ   ከመረብ አሳርፏት 1ለ1 ሆነዋል፡፡ወዲየው በመልሶ ማጥቃት ከአለሚን ከድር የተሻገረትን ኳስ ንጋቱ ሀይሉ ግብ ጠባቂውን አታሎ ወደ ግብ ቀይሯት ጨዋታው 2ለ1ሆኗል፡፡ 41ደቂቃ ሙሉቀን  ከርቀት  የመታት ኳስ የግቡን አናት መታ ወጣለች፡፡    የመጀመሪያ አጋማሽ በዚሁ ውጤት ተጠናቋል፡፡ በሁለተኛ አጋማሽ ሶስት ቅያሪ ዎች በማድረግ  ወደ ሜዳ የገቡት ባለ ሜዳዎቹ ሐዋሳ ከተማዎች በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ግብ በመድረስ  በ49ኛ ደቂቃ ላይ ወንደሰን ሐይሉ ከቅርብ ርቀት  አስቆጥሯት ጫዎታው ሁለት አቻ አድርጎታል፡፡ የማህል ሜዳው ተቅጣጥሮ ኳስን መስርቶ በመጫዎቱ የተሻሉ የነበሩት አዳማ ከተማዎች ይህ ነው የሚባል ሙከራ ማድረግ አልቻሉም በአንፃሩ በጨዋታው የመጀመርያ ደቂቃዎች ጫና የፈጠሩት ሐዋሳ ከተማዎች በ88ተኛው ደቂቃ ሙሉቀን ታደሰ ወደ ግብ ቀይሯት ባለ ሜዳዎቹ  ባለ ድል አድርጓቸዋል፡፡ጨዋታውም በሐዋሳ ከተማ 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...