ድሬዳዋ ከተማ ከስምምነታችን ውጪ ጫና እያደረገብኝ ነው ሲል ግብ ጠባቂው ወንድወሰን አሸናፊ ተናገረ።
ግብ ጠባቂው እንደሚለው “”ከትግራይ ክልል ክለቦች ለመጣነው የተሰጠን ውል ለ6 ወር ነው ነገር ግን ትንሹ የውል ጊዜ አንድ አመት ስለሚል የፈረምነው ለአንድ አመት ነው አሁን ጊዜው በማለቁ ክለቡ ሊለቀኝ ይገባል ደመወዝ ከተከፈለኝም 2 ወር አልፎታል ይህን ማስተካከል አለባቸው” ሲል ተናግሯል።
ውል እያለው ለወላይታ ድቻ ስለመፈረሙ የተጠየቀው ወንድወሰን ” ከድሬዳዋ ጋር ያለኝ ውል በማለቁ ከወላይታ ድቻ ጋር ተስማምቻለሁ ነገር ግን ውሉ ገና አልጸደቀም የኔን መልቀቂያ እየጠበቁ ነው ውሉ ስላልጸደቀ በውል ላይ ውል ፈረመ አያስብልም”ሲል ምላሹን ሰጥቷል።
ክለቡ በበኩሉ ” የትግራይ ክልል ክለቦች ተጨዋቾችን አስፈርመናል ያኔ የነበረው ስምምነት ለአንድ አመት ነው ክለቦቹ ከመጡ ውሉ በ6 ወር ሊጠናቀቅ ተስማምተናል ነገር አሁን ግን ቀርተዋል ስለዚህ ውላችን መከበር አለበት እያልን ነው…አንለቅም ያልነው በህግ ድጋፍ ስላለን ነው” ሲል ተናግሯል።
የክለቡ ሰዎች አክለውም “ከትግራይ ክልል ከመጡ ተጨዋቾች መሃል የማንፈልገው ቢኖር ተጨዋቹ ካልፈቀደ ማሰናበት አትችሉም ተብለን እሄዳለሁ ያለው ተጨዋችስ ያለ እኛ ፍቃድ እንዴት እንዲሄድ ይፈቀዳል? በማለት ይጠይቃሉ።
እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በበኩሉ” ይሄ ጉዳይ አስተዳደራዊ ምላሽ ያስፈልገዋል ተጨዋቹ 6 ወር ነው ውል ያለኝ ማለቱ ልክ ነው ክለቦቹም 6 ወር የተስማማነው የትግራይ ክልል ክለቦች ከመጡ ነው አሁን ካልመጡ ለመልቀቅ አንገደድም ማለታቸውም ስህተት የለበትም በዚህ ክፍተቶች ዙሪያ ጽ/ቤቱ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር ተነጋግሮ አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል”ሲል ገልጿል።
አስተያየት ይስጡ