የአራት ወራት ደመወዝን ያልከፈለው ወልዋሎ ከባድ ችግር ውስጥ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ መወዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየአመቱ በደመወዝ እና መሰል ጉዳዮች በተጫዋቾች በመከሰስ ስመ ጥር መሆን የቻለው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ባለፈው የ2017 የውድድር ዘመን ወደ ሊጉ በድጋሚ መመለስ የቻለ ሲሆን ሲመለስ ግን ከነ ችግሩ ነበር። በያዝነው የ2018 የውድድር ዘመን ከፍተኛ የዝውውር ገንዘብን ካወጡ ክለቦች መካከል አንዱ እንደሆነ ቁጥሮች የሚያመላክተው እና በአሁኑ ሰዓት በወራጅ ቦታ ላይ የሚገኘው ክለቡ ከባድ አደጋ ውስጥ መሆኑን ባደረኩት መረጃ መሰብሰቦች ያገኘውት መረጃ አመላክቷል።
በግለሰቦች የተዝረከረከ ውሳኔ ሰጪነት እስከ አሁን የአራት ወራት ደመወዝን ያልከፈለው ክለቡ የፊታችን የካቲት 14 በሚጀምረው የሁለተኛው ዙር የሊግ ውድድር ከሲዳማ ቡና ጋር መርሀግብር ያለበት ሲሆን አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ ከአስራ አምስት ያነሰ ቁጥር ያላቸውን ብቻ ይዘው ልምምድ በማሰራት ላይ የሚገኙ ሲሆን በዚህም የተነሳ አሰልጣኙ ብስጭት ውስጥ መግባቸው ታውቋል። ደመወዝ አልተከፈለንም ብለው ለፌድሬሽኑ ያመለከቱት ተጫዋቾች ቁጥር ወደ አምስት ሲሆኑ በቅርቡ ደግሞ ሦስት ተጫዋቾች መልቀቃቸው ይታወሳል።
ባለፈውም አመት ተደጋጋሚ ጉዳዮች እየተነሱበት የነበረው እና የክለቡን ባስ ጭሞር በማስያዣነት አሲዞ የነበረው ክለቡ በሊጉ ከባድ ጊዜን በቀጣይ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
- ማሰታውቂያ -
በዚህ ዙሪያ ስለሚለቁ ተጫዋቾች ጉዳይ በቀጣይ ይዤ እመለሳለሁ።


