ሀትሪክ ስፖርት ከወር በፊት የነገረቻችሁ ዜና እውነት ሆኗል።
በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ውስጥ የልጅነት ጊዜውን በስልጠና ካሳለፈ በኋላ በኢትዮ ኤሌክትሪክ በሰበታ ከተማ በኋላም በባህርዳር ከተማ ሲጫወት የምናውቀው አጥቂው አደም አባስ ከሁለት አመት በፊት ባህርዳር ከተማ በሰባተኛ ሳምንት የሊግ ጨዋታውን ከሀዋሳ ከተማ ጋር ለማድረግ ዝግጅት በሚያደርግበት የመጨረሻ ልምምድ ላይ ጉዳት አስናግዶ ለሁለት አመታት ከሜዳ ርቆ መቆየቱን ተጫዋቹም ወደ ጤንነቱ በመመለስ በሁለተኛው ዙር ውሉን ቢያጠናቅቅም ለባህርዳር ከተማ በመፈረም ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ከወር በፊት ጠቁመን የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ወደ በይፋ ወደ ጣናው ሞገድ ተመልሷል።



