በፋይናንስ ህጉ ተጫዋች ማስፈረም ከብዶት የነበረው ኢትዮጵያ መድን ተጫዋች አግኝቷል።
አሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ በፋይናንስ ህጉ የተነሳ ከአርባ እስከ ሀምሳ ሺህ ክፍያ ካልሆነ የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ማስፈረም እንደከበዳቸው የነገሩኝ ሲሆን አሰልጣኙም ባላቸው ቀዳዳ በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለማስፈረም እንደሚገደዱም ጭምር የገለፁ ሲሆን ከሰሞኑ በሙከራ ማስፈረም እጀምራለሁ ባሉት መሠረት የመስመር አጥቂው ሳሙኤል ሳሊሶ ወደ ክለቡ አምርቷል።
እግር ኳስን ከትውልድ ሀገሩ ወንጂ ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ሲከታተል በውድድር ውቅት ባሳየው አቋም በመቻል በመቐለ 70 እንደርታ ሰበታ ከተማ እና ሲዳማ ቡና በመጫወት ቆይታን አድርጎ ከመድን ጋር ከነበረው ጥቂት የሙከራ ቀናት በኋላ ከስድስት ወራቶች በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል።
ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናት አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም የሙከራ ጊዜ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጫለሁ።


