ከአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የዋና ቅጥር አሰልጣኝ በፊት ሸገር ከተማ ረዳቱን ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሊሾም ነው።
አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በማሰናበት በምትኩ ለወራት ከነበረው የስልክ ልውውጥ በኋላ ካሳዬ አራጌን ምርጫቸው በማድረግ ሊቀጥሩት ከጫፍ መድረሳቸው እና ውሳኔን ስለመወሰናቸው ከቀናት በፊት የገለፅን ሲሆን ዛሬ ከክለቡ በተገኘ መረጃ መሠረት አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን ከመቅጠራቸው በፊት ለተወሰኑ ጨዋታዎች ምክትል አሰልጣኙ ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅን በቦታው በጊዜያዊነት ለመሾም የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መደረሱ ተሰምቷል።
የቀድሞው የሀረማያ ዩኒቨርስቲ መምህር በመቀጠልም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፀሐፊ እንዲሁም በአሰልጣኝነት በድሬዳዋ ከተማ ፣ በምክትል አሰልጣኝነት በጅማ አባጅፋር ፣ ፋሲል ከነማ ፣ በሀድያ ሆሳዕና ደግሞ በሁለት አጋጣሚዎች በፋሲል ከነማ እንዲሁም ያለፉትን ስድስት ወራት የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ረዳት አሰልጣኝ ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሲሆን ክለቡ አሁን ፋይናንስ ጉዳይ አኳያ አዲስ አሰልጣኝ ማምጣት ገንዘቡን ከፍ ሲያደርግብን ይችላል የያለውን አሰልጣኝ መመልከት አለብን በማለት ልምምድ ሲያሰሩ የነበሩትን ረዳት አሰልጣኙ ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆነው ሊመሩ እንደሆነ መረጃዎች አመላክተዋል።


