መነሻ ገጽ ወላይታ ድቻ ወላይታ ድቻ ሁለት ወጣት አሰናብቶ ሁለት ዜጋ ተጫዋች አስፈረመ
ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ወላይታ ድቻ ሁለት ወጣት አሰናብቶ ሁለት ዜጋ ተጫዋች አስፈረመ

አጋራ
አጋራ

ከቀናት በፊት እንደጠቆምናችሁ ወላይታ ድቻ ሁለት የውጪ ተጫዋቾችን የግሉ አደረገ።

ከቀናት በፊት አራት ተጫዋቾችን ያሰናበተው ወላይታ ድቻ አሁን ደግሞ ከተስፋ ቡድን ያደጉትን አማካዩቹን አቤኔዘር መኩሪያ እና ቸርነት አበበን በማሰናበት ሁለት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። ከቀናት በፊት ሴኔጋላዊው ግብ ጠባቂ ከሀዲን ኒዲያዬን በማስፈረም የውጪ ተጫዋች አላስፈርምም የሚል ውሳኔውን የለወጠው ክለቡ በዛሬው ዕለት ደግሞ የቤኒን ዜግነት ያለውን የአጥቂ አማካዩን ሳሊፉ ኢብራሂም እና የተከላካይ አማካዩ የናይጄሪያ ዜግነት ያለውን አውግስቲን ኦኬጅፓን የግሉ አድርጓል።

ቤኒናዊው ሳሊፉ ኤልቨን ወንድረርስ እና ህርትስ ኦፎክ ለተባሉ የጋና ክለቦች ዜግነቱን ወደ ቤኒን ከመለወጡ በፊት መጫወት የቻለ ሲሆን በቅርቡ ክለብ አልባ ከመሆኑ በፊት ደግሞ ለኮሶቮው ድሪታ ክለብ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን ሌላኛው የተከላካይ አማካዩ አውግስቲን በበኩሉ ለሀገሩ ናይጄሪያ ክለቦች ዋሪየርስ ፣ ሪቨርስ እና ለታንዛኒያው ሲምባ መጫወት የቻለ ሲሆን ጥቂት ጊዜን ያለ ክለብ ቆይቶ በአሁኑ ሰዓት ለኢራቁ አል ኢትሳላት በመጫወት ላይ ነበር።

ሁለቱም ተጫዋቾች እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ለክለቡ በውድ ክፍያ የፈረሙ ሲሆን ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን ክለቡ በቀጣይ ቀናት ያስፈርማል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...