በአሰልጣኝ ጳዉሎስ ጌታቸዉ(ማንጎ) እየተመሩ የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸውን በሀዋሳ ከተማ እያደረጉ የሚገኙት
ክትፎቹ የቀድሞዉን የኢትዮጵያ ብሐራዊ ቡድን እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረዉን አንጋፋውን የመስመር ተከላካይ አበባዉ ቡጣቆ ወደ ስብስባቸዉ ተቀላቅለዋል።
ረዘም ያሉ አመታትን በፈረሰኞቹ መለያ ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ ተከላካዩ ክለቡን ከለቀቀ በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ ደቡብ ፖሊስ ማምራቱ የሚታወስ ሲሆን ያለፈዉን የ2013 የዉድድር አመት ያለክለብ ካሳለፈ በኋላ አሁን ደግሞ የ2014 የዉድድር አመትን በወልቂጤ መለያ የምንመለከተው ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ