የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ
”የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አማ የውድድር አመራርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ መስከረም 14 እና 19 ቀን 2017 ይግባኝ ባይን አስመልክቶ ያሳለፈውን የዲስፕሊን ውሳኔን ለማሻር የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ” በማለት የይግባኝ ጥያቄያቸውን አስገብተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ሲያጣራ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ያስተላለፈውን ውሳኔ በቀን 19/01/2017 ዓ.ም ለክለቡ ማድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ስለሆነም ተሻሽሎ በወጣው የፌዴሬሽኑ የዲስኘሊን መመሪያ አንቀጽ 98 መሰረት ክለቡ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ገደብ እና ግዴታዎችን ያላሟላ በመሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የሚከተለውን ውሳኔ ወስኗል፡፡

ውሳኔ
1. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ በወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ላይ በወሰነው ውሳኔ ክለቡ ያቀረበው አቤቱታ የይግባኝ ማስገቢያ ጊዜውን ያልጠበቀ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው አልተቀበለውም። ስለሆነም ውሳኔው ፀንቷል፡፡
2. ይግባኝ ባይ ለይግባኝ ያስያዘው ገንዘብ ለፌዴሬሽኑ ገቢ ሆኗል፡፡


