የቀድሞው የቦዲቲ ከተማ ስራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሰብሳቢ ኮሚቴው አዲሱ የጦና ንቦቹ ስራ አስኪያጅ በመሆን ተሹሟል።

በውጤት እጦት መነሻነት አቶ አሰፋ ሆሲሶን ከስራ አስኪያጅነት ካሰናበተ በኋላ በጊዜያዊ ስራ አስኪያጁ ምትኩ ሐይሌ ሲመራ የነበረው ወላይታ ድቻ ውጤታማ ጉዞው ለማስቀጠል በማሰብ አቶ ዋሲሁን ወልደዮሃንስን ዛሬ የክለቡ አዲስ ስራ አስኪያጅ በማድረግ በይፋ መሾማቸውን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጣለች።
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በስፖርት ሳይንስ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የቋጩት አዲሱ ስራ አስኪያጅ የቦዲቲ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ በ2017 እና 2018 የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ እንዲሁም በ2018 ላይ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕርሚየር ሊግ ኮሚቴ በመሆን አገልግለዋል።
አስተያየት ይስጡ