ከደቡብ አፍሪካው ክለብ ጋር ውሉ የተጠናቀቀው ኢትዮጵያዊው አጥቂ አቡበከር ናስር ወደ ቱርክ ሊያመራ መሆኑን ተናግሯል። ለምን የሚለውን በተከታዩ ዘገባ ከራሱ አንደበት ይዘንላችሁ ቀርበናል።

በ2013 የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ይመራ በነበረው ኢትዮጵያ ቡና ውስጥ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባደረገው 24 ጨዋታ 29 ጎሎችን በማስቆጠሩ በበርካታ የአፍሪካ ክለቦች ለመፈለግ የበቃው ኢትዮጵያዊው አጥቂ አቡበከር ናስር በመጨረሻም በደቡብ አፍሪካው ሀያል ክለብ ማሜሎ ዲ ሰንዳውንስ መልየማዮች ዕይታ ውስጥ ፈርሞ በቋሚ አራት አመት ውል አንድ ተጨማሪ አመትን ባካተተ የስምምነት መነሻነት ለክለቡ ለመፈረም መብቃቱ ይታወሳል። በክለቡ ጥሩ አጀማመርን በማድረግ አራት ጎሎችን ማስቆጠር ቢችልም ጉዳት እንደፈለገው መጫወት እንዳይችል ያደረገው ይህ የሊጋችን ባለ ሪከርድ ጎል አስቆጣሪ በመጨረሻም በውሰት ለሌላኛው ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ቢሰጥም በወዳጅነት ጨዋታ ላይ ሌላ ጉዳት አስተናግዶ ሌላ መጥፎ ጠባሳን ለማስተናገድ ተገዷል።
ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ የሚገኘው አጥቂው በተለያዩ የመረጃ አውታሮች ወደ ደቡብ አፍሪካው ክለብ ሰንዳውንስ ተመልሷል ወደ ሌላ አዲስ ክለብ ሊያመራ ከጫፍ ደርሷል አሁን የሚገኘውም ደቡብ አፍሪካ ነው እየተባለ በተደጋጋሚ ቢገለፅም ተጫዋቹ ግን ለሀትሪክ ስፖርት በተለይ እንደተናገረው ውሸት መሆኑን ጠቁሞ። “ገና ነው አልተሻለኝም ዝም ብዬ እዚህ አዲስ አበባ ነው ያለውት ልምምድ እየሰራውኝ ነው ያለውት ትንሽ ይቀረኛል ለማገገም እየሞከርኩኝ ነው”። ነው ሲል የገለፀ ሲሆን ወደ ቱርክ ለህክምና እንደሚያመራ እና ከማሜሎ ዲ ሰንዳውንስ ጋርም ውሌ አልቋል ሲል ተደምጧል። እንደ ሀትሪክ ስፖርት መረጃ ከሆነ ኢትዮጵያዊው ኮከብ በቀጣይ ማረፊያው የኢትዮጵያ ክለብ ሊሆን እንደሚችል ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
አስተያየት ይስጡ