በሰሜን አሜሪካ ነዋሪነታቸው ያደረጉ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በርካታ ለውጥ ያመጣል የተባለ የደጋፊዎች ማህበርን ሊያቋቁሙ ነው።

ኢትዮጵያ ቡናን በተጫዋችነት ፣ በደጋፊነት እና በተለያዩ ጉዳዮች ሲደግፉ የነበሩ አባላትን ያሰባሰበው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማህበር በሚል በቅርቡ ሊመሠረት መሆኑን ለሀትሪክ ስፖርት የደረሳት መረጃ ይጠቁማል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከምስረታው ጀምሮ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ክለቡ በቀጣዮቹ አመታት ክለቡን በፋይናንስ እና በተለያዩ ጉዳዮች ለማገዝ ይረዳ ዘንድ ይህ ማህበር መቋቋም እንደቻለ ታውቋል።
ከኢትዮጵያ ቡና የደጋፊዎች ማህበር ሙሉ ፍቃድን ያገኘውን ይህንን ማህበር የክለቡ የልብ ደጋፊ አቶ ዘነበ ስንታየው ፣ የቀድሞው የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ክፍሌ ወልዴ እና በህዝብ ግንኙነት ክለቡን ባገለገለው ዮሐንስ ዕድሉ ስም ጊዜያዊ ኮሚቴ መቋቋም የቻለ ሲሆን በቀጣይም ኮሚቴዉ ፣ በሚያመቻቸዉ የስብሰባ ቦታ እና ቀን ፣ በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር በሰፊዉ ውይይት እና የሚቋቋመውን ፅህፈት ቤት የሚመሩ አባላት ምርጫ ይደረጋል።
አስተያየት ይስጡ