ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች የተገኘው ተከላካይ።

ቤተሰቦቹ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል በማምራታቸው መወለድ የቻለው በእስራኤሏ አሽዶድ በተባለች ከተማ ውስጥ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ዕድሜውም 24 ሞልቶታል የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዞሀር ዛሳኖ። እግር ኳስን ተወልዶ ዕድገቱን ባደረገባት አሽዶድ ሲሆን ለዚህም ቡድን ከ19 እና በዋናው ክለብም ጭምር መጫወት ተጫውቷል። በመቀጠል ቢታር ጀሩሳሌም በተባለው የሀገሪቱ ፕሪምየር ሊግ ተካፋይ ቡድን በጥሩ አቅም ግልጋሎትን መስጠት ችሏል።

ላለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ዘንድሮ በእስራኤል ፕሪምየር ሊግ አምስተኛ ሆኖ ባጠናቀቀው ማካቢ ሀይፋ ቆይታን እያደረገ የሚገኘው እና ለዕረፍት ኢትዮጵያ እየመጣ የሚመለሰው ይህ ተጫዋች በአውሮፓ ከ21 አመት በታች ዋንጫ እስራኤልን ወክሎ መካፈል የቻለ ሲሆን አንድ ቀን ግን የዋልያዎቹን መለያ በመልበስ የቤተሰቦቹን ሀገር ማገልገል ህልሙ መሆኑን ይናገራል።
አስተያየት ይስጡ