መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ “የምንከተለው የአጨዋወት ፍልስፍናና የአቡኪ ልዩነት ፈጣሪ ተጨዋች መሆን በርካታ ግቦችን እንድናስቆጥር አድርጎናል”ዊሊያም ሰለሞን /ኢትዮጵያ ቡና/
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

“የምንከተለው የአጨዋወት ፍልስፍናና የአቡኪ ልዩነት ፈጣሪ ተጨዋች መሆን በርካታ ግቦችን እንድናስቆጥር አድርጎናል”ዊሊያም ሰለሞን /ኢትዮጵያ ቡና/

አጋራ
አጋራ

በመሸሻ ወልዴ

በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ጥሩ እንቅስቃሴን ከሚያሳዩ ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ቡናው ዊሊያም ሰለሞን የዘንድሮው ውድድር ከሌላው ጊዜ ተሽሎ የሚገኝና ለየት ይላል በተለይ ደግሞ ጎሎች በብዛት እየተቆጠሩ መሆናቸው ፉክክሩን ድምቀት እንዲኖረው እያደረገውም ይገኛል ሲል አስተያየቱን ለሀትሪክ ስፖርት ድረ-ገፅ ሰጥቷል።

ለኢትዮጵያ ቡና ጥሩ አቋሙን በማሳየት ላይ የሚገኘው ዊሊያም ሰለሞን ክለቡ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ከመሪው ፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታውን ከማድረጉ በፊት ከድረ ገፁ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በቡድናቸው በዛሬው ጨዋታ ዙሪያ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ አውርተው ተጨዋቹ ምላሹን ሰጥቷል።

ከፋሲል ከነማ ስለሚያደርጉት የዛሬው ጨዋታ

“ጨዋታውን ከሌሎች ቡድኖች ጋር እንደምናደርገው አንድ አይነት ግምትን ሰጥተን ነው ወደ ሜዳ የምንገባው። እኛ በውድድር ዘመኑ ማንንም ተጋጣሚም አንንቅም። በዛሬው ጨዋታ ጥሩ ፉክክር እንደሚኖር ብናውቅም በስነ-ልቦናው በኩል ጥሩ ስለሆንን ፋሲል በጨዋታ በልጠን እናሸንፈዋለን”።

ፋሲል ከነማ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ከመምራቱ አንፃር የዛሬው ጨዋታ ላይ ይከብዳቸው እንደሆነ

“ፋሲል ከነማ ከሌሎች ቡድኖች አንፃር ጥሩ ቡድን ነው። ኳስንም በደንብ አድርጎ በመጫወት ይለያል። ያም ሆኖ ግን ለእኛ ቡድን የሚጫወት ቡድን ከክብደቱ ይልቅ ይቀለናልና ግጥሚያውን በጥሩ ሁኔታ ነው የምንወጣው”።

ኢትዮጵያ ቡናን ዘንድሮ ስለሚለየው ነገር

“አንድ የአሰልጣኙ በሙያ ብቃቱም ሆነ በሁሉ ነገሩ የተሟላ መሆን መቻሉ ነው። ሌላው ደግሞ እሱ የሚሰጠንን ታክቲክ ሁላችንም የቡድኑ ተጨዋቾች ስለምንቀበል ከዛሬ ነገ ቡድናችን ላይ መሻሻል እንዲኖር አድርጓልና ይሄ ለየት ያደርገናል”።

ስለ ዘንድሮ ግባቸው

“እስከ ዋንጫው ፉክክር እንጓዛለን። አሁን ላይ ምንም ውጤት ሊመዘገብ ይችሏል። ያ እኛን ስጋት ውስጥ ፈፅሞ አይከተንም። ዓመቱ መጨረሻ ላይ ግን ሻምፒዮናው የምንሆነው እኛ ነን”።

በርካታ ግቦችን ስለማስቆጠራቸው

“እነዚህ ግቦች የተቆጠሩበት መንገድ በምንከተለው የአጨዋወት ፍልስፍናችንና በአቡኪ /በአቡበከር ናስር/ ልዩነት ፈጣሪ ተጨዋች መሆን መቻሉ ነው”።

ዊሊያም እና ኢትዮጵያ ቡና

“ሁለቱ አሁን ላይ ገና እየተዋሃዱ ያሉ ናቸው። ቡና ምርጥ እግር ኳስን የሚጫወት ቡድን ነው። እኔ ደግሞ ገና ሙሉ አቅሜን አውጥቼ ያልተጫወትኩ ተጨዋች ነኝና ወደ ቡድኑ አጨዋወት ሙሉ ለሙሉ ዘልቄ ስገባ ለቡድኑ አሁን ከምሰጠው ግልጋሎት በላይም ቡድኑን እንደምጠቅመው አስባለሁ”።

ማሻሻል ስላለባቸው

“ብዙም አለ ብዬ አላስብም”።

በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የተመለከተው ለየት ያለ ነገር

“ከዚህ ቀደም በነበሩት የሊጉ ውድድሮች ብዙ ቡድኖች ከሚከተሉት አጨዋወት የተነሳ ጭምር ጎሎችን አናይም ነበር። ጨዋታዎቹ ወይ 1-0 ይጠናቀቃሉ። ካልሆነ ደግሞ 0-0 ያልቃል። በዚህ ዓመት ግን አንዳንድ ቡድኖች በአጨዋወታቸው ተቀይረው ስለመጡ ጭምር በርካታ ጎሎች እየተቆጠሩ ይገኛልና ይሄ መሆን መቻሉ ለኳሱ ፉክክር ውበት ይሰጠዋል”።

ከኢትዮጵያ ቡና ውጪ የትኛው ቡድንን እንድታደንቅ አድርጎሃል

“ወላይታ ድቻ የእውነትም ጥሩ ቡድን ሆኖ መጥቷል። እነሱን ከእኛ ቡድን በኋላ አድንቄያቸዋለሁኝ። ወልቂጤ ከተማና ሰበታ ከተማም ጥሩ ናቸው”።

ስለ ስብስባቸው

“ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮ የተጨዋቾች ስብስቡ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን በመያዝ ሊጉ ላይ አድናቆትን እያተረፈ ይገኛል። ቡድናችን ውስጥ በብዛት ወጣት ተጨዋቾች ነው የሚገኙት ጥቂት ልምድ ያላቸውም አሉ። የሁለታችን ቅንጅታችንም ጥሩ ነው። እኛ ሜዳ ላይ ስንሳሳት ሲኒየሮቹ እንድንረጋጋ ያደርጉናል። ፍቅርና መከባበር አለ። በዚህ በኩል ቡና ከሁሉም ክለቦች የተሻለ ነውና ይሄን ግንኙነት ነው ለማስቀጠል የምፈልገው”።

ስለ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ

“እሱ የማይታመን አይነት ድንቅ አሰልጣኝ ነው። ከአንተ የጨዋታ ልምድ ይኑርህ አይኑርህ እሱን አያስጨንቀውም የሚፈልገው ወቅታዊ የኳስ ብቃትህን ነው። ካመነብህ ያጫውትሃል። ወጣት ከሆንነው ውስጥ እኔና ሬድዋን እድሉን እያገኘን ያለነው በምንሰራው ስራ አምኖብን ነው። ሌሎቹንም ሲያምንባቸው ያጫውታችኋል። እሱ ጋር መለየት የሚባል ነገር የለም ስለዚህም ለመጫወት ወገብህን ጠበቅ አድርገህ መስራት ነው”።

በመጨረሻ

“ከፋሲል ከነማ ጋር ያለንን የዛሬ ጨዋታ በምንከተለው የጨዋታ ፍልስፍና እናሸንፋለን። ድል ያለ ድል ለክለባችን”።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...