ሀትሪክ፡- የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተከታያችሁን ኢትዮጵያ ቡናን ዛሬ ትፋለማላችሁ፤ ስለ ጨዋታው ምን ትላለህ? ምን ውጤትንስ ትጠብቃለህ?
ሀብታሙ፡- ጨዋታው ለእኛም ሆነ ለእነሱ በጣም ከባድ ነው፤ ከግጥሚያው የሚገኘው ሶስት ነጥብም ለሁለታችንም አስፈላጊያችን ነውና ጥሩ የሆነ የኳስ ፉክክርን እንደምናይ እርግጠኛ ነኝ፤ ከፈጣሪ እርዳታም ጋር ከዚህ በፊት የያዝነውን የአሸናፊነት መንፈሳችንን በማስቀጠል ኢትዮጵያ ቡናን እናሸንፋለን፡፡
ሀትሪክ፡- ኢትዮጵያ ቡና የዛሬ ተጋጣሚያችሁ ከመሆናቸው አንፃር ስለ እነሱ ምን ትላለህ?
ሀብታሙ፡- ኢትዮጵያ ቡና በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙት ቡድኖች መካከል ጥሩ እግር ኳስን የሚጫወት ትልቅ ቡድን ነው፤ እንቅስቃሴያቸው ደስ የሚልና ሊወደድ የሚችልም ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የእናንተው ፋሲል ከነማስ በምን መልኩ ይገለፃል?
ሀብታሙ፡- ፋሲል ደግሞ በጣም አስፈሪና ጠንካራ የሆነ ቡድን ነው፤ ባለፉት 11 ጨዋታዎቹም ያልተሸነፈ እና በምርጥ አቋሙም ላይ የሚገኝ ቡድን ነውና ይሄን አስፈሪ ቡድንነቱን በቀጣዮቹ በርካታ ጨዋታዎቹም ላይ ይቀጥልበታል፡፡
ሀትሪክ፡- ቅ/ጊዮርጊስን ከብዙ ትንቅንቅ በኋላ መጨረሻው ሰዓት ላይ ባገኛችሁት የፍፁም ቅጣት ምት አሸንፋችሁት ነበር፤ በዛ ጨዋታ ዙሪያና ስለ ፍፁም ቅጣት ምቷ ምን ትላለህ?

ሀብታሙ፡- ከቅ/ጊዮርጊስ ያደረግነው ያለፈው ሳምንት ጨዋታ ለእኛ በጣም ፈታኝ ነበር፤ እኛ የ5 ነጥቡን ልዩነት ለማስፋት እነሱ ደግሞ ልዩነቱን ለማጥበብ ያደረግነው ስለነበር ጨዋታው እልህና ጉሽሚያ ነበረበት፤ ፈጣሪም ይመስገንና ያ ጨዋታ አቋማችንን በደንብ ያሳየንም ግጥሚያ ነው፤ በጨዋታው ቆይታችን ሁለታችንም ቡድኖች ለመሸናነፍ ጥሩ ፉክክርንም አድርገንበታል፤ ማመን እስኪያቅተን ድረስም ነው በመጨረሻው ሰዓት ላይ ያሬዳ ባየህ ባስቆጠረው የፍፁም ቅጣት ምት ግብ እነሱን አሸንፈናቸው ከሜዳም የወጣነው፤ ከዛ በፊት በነበሩት ሰዓታቶች ግጥሚያውን በአቻ ውጤት ልናጠናቅቅ ነው ብለን አስበንም ነበር፤ በመጨረሻ ላይ ግን ፈፅሞ ባልጠበቅነው ሰዓት ሪጎሬ አግኝተን የአሸናፊነቱን ግብ ስናስቆጥር እኔም ሆንኩ የቡድን ጓደኞቼ ስሜታችንን መቆጣጠር አቅቶንም ነበር፤ የፍፁም ቅጣት ምቱን በተመለከተ ዳኛው ተገቢ የሆነ ውሳኔ ነው የወሰነው፤ አስቻለው ታመነ በአጥቂያችን ፍቃዱ ላይ ፋውልን ሰርቶበታል፤ ከህጉ አንፃርም ያ ፍፁም ቅጣት ምት የሚያሰጥም ሆኗል፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሲጠናቀቅ የት ደረጃ ላይ ይገኛል?
ሀብታሙ፡- በሊጉ ላይ ያለንን ተሳትፎ አስመልክተን ቡድናችን የት ድረስ ሊጓዝ እንደሚችል ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ያደረግነው ጨዋታ ብዙ ነገርን ሊያስመለክተን ችሏል፤ ጠንካራ ቡድን እንደሆንም ታይቷል፡፡
ሀትሪክ፡- ለፋሲል ከነማ ግብን መች ያስቆጥር እንደሆነ?
ሀብታሙ፡- እውነት ነው፤ ለቡድኔ ጎሎችን ማስቆጠር አለብኝ፤ ይሄን ደግሞ ወይ ዘንድሮ ካልሆነ በመጪው ዓመት ላይ የማሳካው ነው የሚሆነው፡፡
ሀትሪክ፡- በቤት ኪንጉ ከእናንተ ቡድን ውጪ ሌላ ምርጥ ቡድንን ማንን ተመለከትክ?
ሀብታሙ፡- ብዙ አሉ፤ በዋናነት የምጠቅሳቸውም ቡናን ቅ/ጊዮርጊስን፣ ወልቂጤ ከተማንና ባህርዳርን ነው፡፡
ሀትሪክ፡- በመጨረሻ..?
ሀብታሙ፡- በእግር ኳሱ አሁን ላይ ለደረስኩበት ደረጃ በዋናነት የረዳችኝን ሁሌም ደግሞ ስሟን ከፍ አድርጌ የማነሳትን እና መሰረቴ የሆነችውን የጌታዬ እናት ድንግል ማሪያምን በጣም ላመሰግናት እፈልጋለውኝ፡፡
“ፋሲል ከነማን የምንፋለምበት ጨዋታ ብዙም አይከብደንም፤ ማሸነፋችንም አይቀርም” አቡበከር ናስር /ኢት.ቡና/
አስተያየት ይስጡ