ባሳለፍነው ሳምንት በልደታ ክፍለ ከተማ ማራኪ እንቅስቃሴ ያደረገውን አሰልጣኝ ኤርሚያስን መቅጠር የቻሉት ኢትዮ ኤሌትሪኮች ወደ ዝውውር በመግባት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ረዥም ዓመታትን በግብ ጠባቂነት መጫወት የቻለችው ንግስት መዓዛ ለ አንድ ዓመት ያልተጣራ ወራዊ ደሞዝ 152,586.00 ማስፈረም ችሏል ።
የሴካፋ ዞን አሸናፊዎቹ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አንድ ተጨዋቾች ሲያስፈርሙ የአንድ ተጨዋች ውል አራዝሟል ።
በዛሬው እለት ፍርማዋን ያኖረችው የሀዋሳ ከተማ ተጨዋች የነበረችው ትግስት አዳነ ስትሆን ወራዊ ያልተጣራ ደሞዝ 221,551.00 የሚከፈላት ይሆናል ። ቅድስት ዘለቀ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በሻምፒዮናዎቹ ቤት ለመቆየት የተስማማች ሁለተኛዋ ተጨዋቾች መሆን ችላለች። ቅድስት በ ወር ያልተጣራ ደሞዝ 247,413. የሚከፈላት ይሆናል ።


- ማሰታውቂያ -


