ኢትዮጵያ ቡና ባለፉት ወራት ላይ የቡድን ምክትል አሰልጣኝ የነበረውን አሰልጣኝ አብይ ካሳሁንን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።
ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ አሳውቃለሀ ያለው ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኙ ለምን ያህል ጊዜ እንደተዋዋለ አልገለፀም።
ክለቡ ፌዴሬሽኑ ባወጣው አስገዳጅ የክለብ ላይሰንሲንግ መስፈርት መሰረት ከአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ ጋር መቀጠል እንዳልቻለም አስታውቋል።
አዲሱ ዋና አሰልጣኝ አብይ ካሳሁን አስቀድሞ የክለቡ የ20 ዓመት በታች አሰልጣኝ በመሆን ዋንጫ ማሳካት መቻሉ ይታወሳል።
- ማሰታውቂያ -




