በአዳማ ከተማ ዝግጅት የጀመሩት ንግድ ባንኮች ሁለት ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ኮከቦችን ጨምሮ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ።
በዛሬው ዕለት ማረፊያቸውን በአዳማ ከተማ ካኖፒ ሆቴል በማድረግ ለሴካፋ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ዝግጅታቸውን የጀመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ከቀናት በፊት የአራት ነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት ማራዘሙ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም ተጨማሪ ተጫዋቾችን በቀጣይ ቀናት እንደሚያስፈርም ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ግብ ጠባቂዋ ገነት ኤርሚያስ የክለቡ አዲሷ ፈራሚ ሆናለች። ከሾኔ ከተማ ከተገኘች በኋላ ለሀዋሳ ከተማ ፣ አርባምንጭ ከተማ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ልደታ እና የተጠናቀቀውን አመት ደግሞ በባህርዳር አሳልፋ ቀጣይ መጃረሻፋ ቻምፒዮኖቹ ቤት ሆኗል። ሌላኛዋ ፈራሚ የመስመር አጥቂዋ የምስራች ላቀው ናት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫውታ ያሳለፈችው የቀድሞዋ የአርባምንጭ ከተማ ፣ መቻል ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ያለፉትን ሁለት አመታት ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ከተጫወተች በኋላ በድጋሚ ወደ ቀድሞው ክለቧ ከአመታት በኋላ ተመልሳለች።
ሁለቱ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችም ማረፊያቸው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሆኗል። በብሔራዊ ቡድኑ በተደጋጋሚ ጎሎችን በማስቆጠር ስሟን በአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ያስጠራችው ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በኋላ በቦሌ ክፍለ ከተማ ያሳለፈችው አጥቂዋ ምህረት አየለ እና የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የአመቱ ምርጥ ጎል አስቆጣሪ አሸናፊዋ እና ከ17 አመት ብሔራዊ ቡድን ሌላኛዋ ኮከብ አጥቂዋ ሊዲያ እያሱ ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ወደ ንግድ ባንክ ያመሩ አራት ተጫዋቾች ሆነዋል።
አስተያየት ይስጡ