መነሻ ገጽ ዜናዎች የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር ከክለቦች ጋር ሊወያይ ነው
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር ከክለቦች ጋር ሊወያይ ነው

አጋራ
አጋራ

በተጫዋቾች የክፍያ ጣሪያ ላይ አዲስ ውሳኔን ለማሳለፍ የፊታችን ዕሁድ ውይይት ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የክለቦችን የተጫዋቾች የክፍያ ጣሪያን ከፍ ለማድረግ አልያም ደግሞ ገደቡን ሙሉ በሙሉ ለማንሳት ከክለቦች ጋር ውይይት ለማድረግ በቀጣዩ ሳምንት ዕሁድ ሐምሌ 19/2018 ቀጠሮ መያዙን ሃትሪክ ስፖርት ያገኘው መረጃ ያመላክታል። ክለቦች ለተጫዋቾች የሚከፍሉትን ገንዘብ በተመጣጠነ መልኩ ተከትለው መክፈል አለባቸው በሚል በመጀመሪያ 56 ሚሊዮን በአመቱ ደግሞ ህጉ ተሻሽሎ 70 ሚሊዮን ብር የአንድ ክለብ አመታዊ በጀት እንዲሆን በመወሰን ወደ ስራ ቢገባም ክለቦች ህጉን ተፈፃሚ ከማድረግ አኳያ ግን ክፍተቶች ነበሩባቸው። የወጣውን ህግ በማይፈፅሙ ክለቦች ላይ ደግሞ ቅጣትን ለመጣል የፋይናንስ አጣሪ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ተግባር ቢገባም አክሲዮን ማህበሩ ግማሹን ቀጥቶ ገሚሱን በዝምታ ማለፉ በርካቶችን እንዳሳዘነ ይታወሳል።

ይህንን ጉዳይ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ ለማበጀት ትላንት ዕሁድ ሐምሌ 12 የፕሪምየር ሊጉን ክለቦች በመጥራት የፋይናንስ ገደቡ ይነሳ ወይም የገንዘብ መጠኑ ከፍ ይበል በሚለው ጉዳይ ለመወያየት አቅዶ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አቶ ኢሳያስ ጂራ ለአለም ዋንጫ ፍፃሜ ወደ አሜሪካ በማምራታቸው ምክንያት ቀኑ በአንድ ሳምንት መገፋቱ ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...