ሰርቪያዊው አሰልጣኝ ቀጣዩ የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ለመሆን ተቃርበዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስን ከአመታቶች በፊት በሁለት አጋጣሚዎች ማሰልጠን የቻሉት እና አምስት ጊዜም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ያደረጉት ሰርቪያዊው አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊት ሚቾ ቀጣዩ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ሆነው ለሦስተኛ ጊዜ በቅርቡ እንደሚሾሙ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። የአልጄሪያውን ኢ ኤስ ስቲፍን ከለቀቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የቀድሞው ክለባቸው ቅዱስ ጊዮርጊስን ከነበረበት መጥፎ ቅርቃር ለማላቀቅ ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጎን በመሆን በብርቱ የታገሉት አሰልጣኙ የቱኒዚያውን ሲ ኤፍ ሴፋክሲያንን ይቀላቀላሉ ተብሎ ቢጠበቅም ቀጣዩ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አስተያየት ይስጡ