ኢትዮ ኤሌክሪክ የአሰልጣኙን ውል ሲያራዝም አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም እና የዘጠኝ ነባሮችን ውል አራዝሟል።
በአሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ መሪነት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው እና በነሀሴ ወር መጀመሪያ ወደ ዝግጅት የሚገባው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአሰልጣኘሰ ኤርሚያስ ዱባለን ውል ለሁለት ተጨማሪ አመት ሲያራዝም አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ የዘጠኝ ነባር ተጫዋቾችን ውል ደግሞ ማራዘሙን ክለቡ ለሃትሪክ ስፖርት በላከልን መረጃ ለመመልከት ችለናል።

የቀድሞው የንግድ ባንክ እና ሀዋሳ ከተማ አማካይ ሲሳይ ገብረዋህድን ጨምሮ መሠረት ወርቅነት የመስመር ተከላካይ ከንግድ ባንክ ፣ አበባየው ጣሰው ግብ ጠባቂ ከመቻል ፣ ቤተልሄም መንተሎ አማካይ ከመቻል ፣ ሚቴ ረታ ግብ ጠባቂ ከልደታ ፣ ረድኤት ክንዴ የተከላካይ አማካይ ከልደታ ፣ ሚለን ጋየን አማካይ ከቦሌ ፣ ሂሩት ተስፋዬ የተከላካይ አማካይ ከንግድ ባንክ ፣ ታሪኬ ጴጥሮስ አጥቂ ከሀዋሳ ከተማ እና የመስመር ተከላካዩዋ ለምለም አሰታጥቄ ከሀዋሳ ከተማ ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲሶቹ ፈራሚ ተጫዋቾች ሆነዋል።

ውላቸውን ያራዘሙ ዘጠኙን ተጫዋቾች ስንመለከት ፀጋነሽ ወራና አጥቂ ፣ ትዕግሥት ያደታ አማካይ ፣ ንግስቲ መአዛ ግብ ጠባቂ ፣ ቤተልሄም በቀለ ተከላካይ ፣ ባንቺይርጋ ተስፋዬ ተከላካይ ፣ ገብሬላ አበበ አማካይ ፣ ብርሀን ሀይለስላሴ አጥቂ ፣ ህዳት ካሱ አጥቂ እና እየሩስ ወንድሙ አጥቂ ናቸው።

አስተያየት ይስጡ