መነሻ ገጽ ሸገር ከተማ ሸገር ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር እንደሚቀጥል ታውቋል
ሸገር ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ሸገር ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር እንደሚቀጥል ታውቋል

አጋራ
አጋራ

ሸገር ከተማን በጊዜያዊ እና ዋና ሚና እየመሩ አመቱን የቋጩት አሰልጣኝ ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት ደርሰዋል።

በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ በማደግ የተካፈለው ሸገር ከተማ አመቱን በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቢጀምርም አሰልጣኙን ከውጤት መጥፋት ጋር በተገናኘ በማሰናበት ረዳት አሰልጣኝ የነበሩትን ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅን በጊዜያዊ እና በመጨረሻም በዋና አሰልጣኝነት ሚና በመሾም አመቱን አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ እንዲያጠናቅቅ አድርገዋል። የቀድሞው የሀሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህር ፣ የድሬዳዋ ከተማ የቴክኒክ ዳይሬክተር እንዲሁም በሀድያ ሆሳዕና ጅማ አባጅፋር እና ፋሲል ከነማ በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት አሰልጣኝ ያስመዘገቡት ውጤት አመርቂ መሆኑን ተከትሎ ሌሎች ጉዳዮችም ተካተው አሰልጣኙ በክለቡ የቀጣይ አመት በዋና አሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ ክለቡ ከአሰልጣኙ ጋር መስማማታቸውን ሀትሪክ ስፖርት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...