ሲሳይ ገ/ዋህድ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች !
የኢትዮጵያ ሴቶች እግርኳስ ሽልማት በዛሬዉ ዕለት ካሳንችስ አካባቢ በሚገኘዉ በጁፒተር ሆቴል በርካታ የኢትዮጵያ እግእኳስ ፌደሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና የክብር እንግዶች በተገኙበት ከናውኗል ፤
- ማሰታውቂያ -
በዚህም መሰረት :-
#በኢትዮጵያ_ፕሪምየር_ሊግ
– የአመቱ ኮከብ አሰልጣኝ :- ብርሀኑ ግዛዉ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
– የአመቱ ምርጥ ተጫዋች :- ሲሳይ ገ/ዋህድ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ
– የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ :- አበባ አጄቦ ከአዲስአበባ ከተማ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆንም ሴናፍ ዋቁማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሸላሚ መሆን ችላለች።
#በከፍተኛ_ሊግ
– የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ :- እንዳልካቸዉ ጫካ ከቂርቆስ ክ/ከተማ
– የአመቱ ምርጥ ተጫዋች :- ድርሻየ መሐመድ ከቂርቅስ ክ/ከተማ
– የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ :- ልዩወርቅ መንበረ ከባህርዳር ከተማ
በከፍተኛ ሊጉ ውድድርም አመቱን በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ማጠናቀቅ ለቻሉት የፋሲል ከነማዋ ቤተልሄም እና ለሞጆ ከተማዋ ምህረት ታፈሰ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በተጨማሪም በዕለቱ ኮከብ ተብለዉ ለተሸለሙት ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች እንዲሁም ምስጉን ዳኞች እንደየደረጃቸዉ ከ40,000 ብር ጀምሮ እስከ 75,000 ብር ድረስ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።