የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬዉ ዕለት ባደረገዉ ስብሰባ የተለያዩ ወሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን ፤ ከነዚህ መካከልም የተጫዋቾች ዝውውርን በተመለከተ የሊጉ ክለቦች ማዘዋወር የሚችሉት የውጪ ተጫዋች ብዛት ከሶስት ወደ አምስት ከፍ እንዲል ዉሳኔ አሳልፏል።
በዉሳኔዉ መሰረትም ክለቦች የሚያስፈርሙት ተጫዋች ከአፍሪካ ከሆነ በዋና ሊግ ደረጃ የሚጫወት መሆን እንዳለበት ሲገለፅ ፤ ነገር ግን ከአፍሪካ ውጭ ከሆነ በየትኛዉም የሊግ ዕርከን የሚጫወት ተጫዋች ክለቦች ማስፈረም እንደሚችሉ ተገልጿል። በተያያዘም ክለቦች በአንድ ጨዋታ ያለገደብ የውጭ ዜጋ ተጫዋቾችን ማጫወት እንደሚችሉ ተቀምጧል።