መነሻ ገጽ ዜናዎች የሴቶች አሰልጣኞች የሙያ ማህበር ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጋር በጋራ የሰጡት ስልጠና ተጠናቀቀ
ዜናዎችየሴቶች ከፍተኛ ሊግየሴቶች ፕሪምየር ሊግየኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ

የሴቶች አሰልጣኞች የሙያ ማህበር ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጋር በጋራ የሰጡት ስልጠና ተጠናቀቀ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ የሴት እግር ኳስ አሰልጣኞች ማህበር ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጋር በቅንጅት የሰጡት ስልጠና ተጠናቀቀ።

በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኞች ማህበር እና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የጋራ ትብብር ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታና የእውቀት ልውውጥ የስልጠና መርሀግብር በመልካ አዳማ ሆቴል በአዳማ ከተማ ሲደረግ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል። በትላንትናው ዕለት ጅምሩን ባደረገው ይህ የስልጠና መርሀግብር በመጀመሪያው ቀን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በአሰልጣኝ ማዕደር እንየው ስለ (Periodization preseason and Tactics) እንዴት ሊታቀድና ሊተገበር ይችላል በሚለው ርዕስ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን የሙያ ማህበሩ አባላትም በአምስት ርዕሶች ላይ በግሩፕ በመሆን ውይይትና የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ተደርጓል።

በዛሬው የመዝጊያ ቀንም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በአሰልጣኝ ሀብታሙ ዳዲ (Soccer game management) በሚል ሰፋ ባለ ርዕስ ስልጠናው መሰጠት የቻለ ሲሆን ከስልጠናው መጠናቀቅም በኋላ ሰፊ የውይይት እና የመከራከሪያ ሀሳቦች ተሰንዝረው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዘለግ ያሉ ውይይቶች ተከናውኖ ጉባኤው የሁለት ቀናት ስልጠናውን ዛሬ ቋጭቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...