የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የደቡብ ሱዳኑ ክለብ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ?

ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከላይቬሪያው ክለብ ሊስከር የጥቂት ጊዜያት ቆይታ በኋላ ወደ ደቡብ ሱዳን አምርተው ጃሙስን ክለብን ሲያሰለጥኑ ቆይተዋል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ደደቢት ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከነማ አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቆይታ በኋላ በፋሲል ከነበራቸው ቆይታ መልስ ወደ ደቡብ ሱዳን እንዳመሩ ይታወሳል። የደበብ ሱዳኑን ክለብ ጃሙስን ብራዚላዊውን ሪካርዶን ተክተው በአንድ አመት ውስጥ አምስተኛ አሰልጣኝ መሆን ችለው የነበሩት ኢትዮጵያዊው ሰው በቅርቡ በደቡብ ሱዳን ፕሪምየር ሊግ ከሜዳቸው ውጪ ያስተናገዱት ሽንፈትን ተከትሎ ቀሪ ጨዋታዎች በሊጉ እየቀረ ኤልሜሪክ ቦንቱ ክለብ ቻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል።
በሀገሪቱ ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የአሰልጣኝ ውበቱ አባተው ክለብ ባለቤት በተደጋጋሚ በግሉ በሚወስናቸው ውሳኔዎች የተነሳ የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ማምጣት እንዳልቻሉ በነበረኝ ቆይታ የገለፁልኝ አሰልጣኙ በአሁኑ ሰዓት ክለቡ በዛው ሀገር ባሉ አሰልጣኞች መሰልጠን የጀመረ ሲሆን አሰልጣኙ በስራ ላይ አመሆናቸውን ጠቁመውናል። አሰልጣኙ በስልክ እንዳሉኝ ከሆነም ቀሪ ኮንትራት ሰሰላለኝ ከክለቡ ጋር ቁጭ ብለን ስለመለያየትም ሆነ ስለሌሎች ጉዳዮች ያወራነው ነገር የለም ያሉኝ ሲሆን አሰልጣኙ እና በረዳት አሰልጣኝነት የወሰዷቸው ፋንታዬ አባተ እና መብራሀቱ ሀብቱም አሰልጣኙን ተከትሎ በስራ ላይ የሌሉ ባለሙያዎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
አስተያየት ይስጡ