መነሻ ገጽ ዜናዎች የሊጉ የመጨረሻ ቀን ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ የመጨረሻ ቀን ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አጋራ
አጋራ

በሳምንቱ የመጨረሻ ቀን የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለ ጎል ሲፈፅም የባህርዳር እና ምድረገነት ሽረ ጨዋታ 1ለ1 ተፈፅሟል።

ዝናባማ በነበረው የአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያገናኘው ጨዋታ ያለ ጎል 0ለ0 ተጠናቋል። በንፅፅር ሲዳማ ቡና የተሻሉ ሆነው በቀረቡበት ጨዋታ በርከት ባሉ ደጋፊዎች ፊት ቢደረግም ጎልን አላስመለከተንም ይልቁንም ሲዳማ ቡና ከተከታዩ መቻል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስምንት ሲያሰፋ ፈረሰኞቹም ደረጃቸውን ወደ አስረኛ አሳድገዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በነበረ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ከ ምድረገነት ሽረ ጋር 1ለ1 ማጠናቀቅ ችለዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ በተቆጠሩ ጎሎች እና ባህርዳር ከተማዎች የተሻሉ በነበሩበት መርሀግብር 21ኛው ደቂቃ ላይ አቤል እንዳለ ላይ አማኑኤል ገብረሚካኤል በሰራው ጥፋት ወደ ቀኝ ካደላ ቦታ የተሰጠውን የቅጣት ምት ተካልኝ ደጀኔ ሲያሻማ ስኔጋላዊውን የግብ ዘቡ ፔፕ ሰይዶን ተክቶ የገባው ይገርማል መኳንንት በሰራው ግላዊ ስህተት በራሱ ላይ በማስቆጠር ምድረገነት ሽረ መሪ ሲሆን 37ኛው ደቂቃ ላይ በተሻለ ብልጫን የወሰዱት ባህርዳሮች ፍቅረሚካኤል አለሙ በጥሩ ዕይታ የሰጠውን ኳስ አንተነህ ተፈራ በጥልቀት ገብቶ ወደ ጎል ሞክሮ የግቡ የቀኝ ቋሚን ገጭታ ኳሷ ስትመለስ ሠለሞን ገብረክርስቶስ በራሱ መረብ ላይ ሳያስብ ነክቶ ያረፈችው ኳስ ጨዋታው 1ለ1 መጠናቀቅ እንዲችል ሆኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...