መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰርቪያዊው ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ መጥተዋል
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሰርቪያዊው ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ መጥተዋል

አጋራ
አጋራ

ከፈረሰኞቹ ጋር አምስት የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሱት ሰርቪያዊው አሰልጣኝ ወደ ቀድሞው ክለባቸው ተመልሰዋል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ከታዩ ድንቅ የውጪ ዜጋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ መሆን የቻሉት ሰርቪያዊው አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊት ሚቾ ወደ ቀድሞው ክለባቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአማካሪነት መመለሳቸውን አውቀናል። አስራ ሁለት ክለቦችን እና አምስት ሀገራት ደግሞ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ መሰልጠን የቻሉት አሰልጣኙ እንደ ኦርላንዶ ፓይሬት ፣ ያንጋ አፍሪካ ፣ አልሂላል እና ዛማሌክ ያሉ የአፍሪካ ስመ ጥር ክለቦችን ማሰልጠን ቢችሉም እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ስኬታማ የሆኑበት ቡድን የለም ከ1997 እስከ 2002 ክለቡን ያሰለጠኑት አሰልጣኙ በፈረሰኞቹ ቤት አምስት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫዎችን ያነሱ ሲሆን አንድ የጥሎ ማለፍ ዋንጫን ከክለቡ ጋር ማንሳት ችለዋል።

ትላንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የፕሪምየር ሊጉን ጨዋታዎች ሲመለከቱ የነበሩት እና በቅርቡ በአልጄሪያ ሊግ ከሚወዳደረ ኢ ኤስ ስቲፍ ጋር በመለያየት ለዕረፍት ትዳር ወዳገኙባችፈት ኢትዮጵያ የመጡት አሰልጣኝ ሚቾ እስከ ውድድር ዘመኑ ፍፃሜ ድረስ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ በጨዋታ እና ከጨዋታ ውጪ የቀድሞው ክለባቸውን እያገዙ አመቱን እንደሚቆዩ የሰማን ሲሆን እንዳገሁት መረጃ ከሆነ ግን ከሌሎች የአፍሪካ ክለቦች ጋር ንግግር ላይ የሚገኙት አሰልጣኙ የቅዱስ ጊዮርጊስን የፋይናንስ ስርዓት መሻሻልን ተከትሎ ጥሩ ክፍያን የሚያገኙ ከሆነ ቀጣዩን አመት በክለቡ የዋና አሰልጣኝነት ሚና ልናያቸው እንደምንችልም ማወቅ ችያለሁ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...