33ኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር የሶስት ቀናት እድሜ ብቻ ቀርተውታል።
በዉድድሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑት ዋልያዎቹም ከአስራ ሁለት ቀናት በፊት ቀደም ብለዉ ወደ አዘጋጇ ሀገር ካሜሩን በመጓዝ ዝግጅታቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን ፤ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውንም የፊታችን ዕሁድ በዉድድሩ መክፈቻ ዕለት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ ከኬብ ቨርዲ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።
ከዚያ አስቀድሞ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ከካፍ ኦላይን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል:-
”እኛ ከባድ ምድብ ውስጥ ነን። አስተናጋጇ ካሜሩንም በምድባችን ነዉ የምትገኘዉ ፤ ወደ ውድድሩ የመጣነዉ ለተሳትፎ ብቻ ሳይሆን ወደ ሚቀጥለው ዙር ለማለፍ ነዉ። ለዚህም የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን። 99% የሚሆነው የቡድናችን ስብስብ ከሀገር ዉስጥ ሊግ የተመረጡ ናቸዉ። ነገርግን በአብዛኛው ወጣት እና ተስፋ ሰጪ ቡድን አለን። ”
ከአሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ቀድም ብሎ ከካፍ ኦላይን ጋር አጠር ያለ ቆይታን ያደረገዉ አምበሉ ጌታነህ ከበደ ደግሞ በእግርኳስ ማድረግ የማይቻል ምንም ነገር እንደሌለ እንዲሁም በዉድድሩ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴን ለማሳየት እንዲሁም ጨዋታዎችን በትኩረት ለመከወን ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ የገለፀው አጥቂዉ በአፍሪካ ዋንጫው ላይም ግብ ለማስቆጠር እንደጓጓ ገልጿል።
በዉድድሩ ላይም ከዋልያዎቹ ስብስብ ዉስጥ አቡበከር ናስር ፣ ጌታነህ ከበደ እና ሱራፌል ዳኛቸዉ ተጠባቂ ተጫዋቾች እንደሆኑ ካፍ ኦላይን አስነብቧል።
አስተያየት ይስጡ