በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚደረገው የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች መደረግ ጀምረዋል።
በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ከዚምባቡዌ አቻው ተድልድሎ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚው ራሱን ከማጣሪያው በማግለሉ ወደ 2ኛው ዙር ማለፉም የሚታወስ ነው።
በአሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ የሚመራው ቡድኑ በ2ኛው ዙር የማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ ከካሜሩን አቻው እንደሚጫወትም ተረጋግጧል።
የካሜሩን የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን ትናንት ምሽት አስተናግዶ 1 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን በድምር የ6 ለ 0 ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ እና የካሜሩን የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ካሜሩን ላይ ከየካቲት 28 – 30 የመልሱን ደግሞ ከመጋቢት 5 – 7 ባሉት ቀናት መካከል በኢትዮጵያ ያደርጋሉ።
የዚህ ጨዋታ አሸናፊ በመጨረሻው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ የናሚቢያ እና የዩጋንዳ አሸናፊን ይገጥማል።


