By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሉን ሲያስቀጥል አርባምንጭ ከተማም አሸንፏል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ድሬዳዋ ከተማአርባምንጭ ከተማስሁል ሽረየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሉን ሲያስቀጥል አርባምንጭ ከተማም አሸንፏል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 1 year ago
Share
SHARE

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በጥምቀት ዋዜማ በዕለተ ከተራ መደረግ ጀምረዋል።

በሳምንቱ ቀዳሚ ጨዋታ የፋሲል ተካልኙ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአ.ሳ.ቴ.ዩ ስታድየም ያለውን የማሸነፍ ግስጋሴ ያስቀጠለበትን ድል በድሬዳዋ ከተማ ላይ ተቀዳጅቷል።

2 – 0 በሆነ ውጤት በተጠናቀቀው ጨዋታ የድሬዳዋ ከተማው አብዱል ጋንዩ በራሱ መረብ ላይ እንዲሁም ፍፁም ጥላሁን ከዕረፍት መልስ የፈረሰኞቹን ግብ ከመረብ አሳርፈዋል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ድል በሁለቱ ክለቦች የእርስ በርስ ግንኙነት ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ የተመዘገበ ነው።

- ማሰታውቂያ -

ፍፁም ጥላሁን የውድድር ዓመቱን 6ኛ የሊግ ግብ በማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አስቀጣሪነቱን በጥምር የሚመሩትን ተጫዋቾች መቀላቀል ችሏል።

ባለፉት ሁለት አመታት በባህርዳር ከተማ ቆይታ የነበረው ፍፁም በሁለቱ የውድድር ዘመናት በድምር ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛቶች ለመስተካከል ሁለት ግብ ብቻ ቀርቶታል።

ተከታታይ አራተኛ ጨዋታውን በአ.ሳ.ቴ.ዩ ስታድየም ያሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመሪው መቻል ጋር በአንድ ነጥብ ርቀት ብቻ ተቀምጧል።

በዚህ ስታድየም ምንም ሽንፈት ያላስተናገደው የሊጉ የ16 ጊዜ ሻምፒዮን በ33ኛ ጨዋታው ያስተናገደው 24ኛ ድሉ ሆኗል።

የይታገሱ እንዳለው ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ ተከታታይ አምስተኛ ድል አልባ ጉዞው የቀጠለበትን ሽንፈት አስተናግዷል።

ቡድኑ ባለፉት አራት ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ የአቻ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን ሽንፈቱም ከ73 ቀናት በኋላ የተመዘገበ ነው።

በተለይም መሐመድኑር ናስርን ካጣ በኋላ በፊት መስመር እየተቸገረ ያለው ድሬዳዋ ከተማ አጥቂውን በጉዳት ካጣ በኋላ ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አንድ ግብ ብቻ አስቆጥሯል።

በ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን ሲገጥም ድሬዳዋ ከተማ አራፊ ቡድን ነው።

በዕለቱ ሁለተኛ መርሐግብር ስሁል ሽረ ከአርባምንጭ ከተማ ተገናኝተው አዞዎቹ 1 – 0 ረተዋል።

ለበረከት ደሙው ቡድን ቡታቃ ሸመና በ73ኛ ደቂቃ ላይ ብቸኛውን ግብ ከመረብ አሳርፏል። ቡድኑ ባሳለፍነው ሳምንትም አዳማ ከተማን 2 – 0 አሸንፎ እንደነበር አይዘነጋም።

ስሁል ሽረ በበኩሉ ድሬዳዋ ላይ መቀሌ 70 እንደርታን ከረታበት ጨዋታ በኋላ በአ.ሳ.ቴ.ዩ ስታድየም ተከታታይ አራተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በቀጣይ ሳምንት መርሐግብር አርባምንጭ ከተማ ከወላይታ ድቻ እንዲሁም ስሁል ሽረ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይጫወታሉ።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የሉሲዎቹ አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ታውቋል
Next Article የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ተጋጣሚውን አውቋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግሲዳማ ቡናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

ሲዳማ ቡና አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

kidus Yoftahe By kidus Yoftahe 5 years ago
ኢንተናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ አቀባበል ተደረገለት !
ታደለ መንገሻ ወደ ሰበታ ከተማ አምርቷል
“መልክህ አላማረኝም ብለው የተነሱ ደጋፊዎች ቢኖሩም ሁሉንም
በውጤት ለማሳመን ጠንክሬ እየሰራሁ ነው”አሰልጣኝ ስዩም ከበደ (ፋሲል ከነማ)
ሳምንታዊዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?