መነሻ ገጽ U -17 ብሄራዊ ቡድን የምንሄደው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች አቅም ለአለም ለማሳየት ነው” አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር
U -17 ብሄራዊ ቡድንዜናዎች

የምንሄደው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች አቅም ለአለም ለማሳየት ነው” አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር

አጋራ
አጋራ

የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቶ በመቋጨት ዛሬ ሌሊት ወደ ሞሮኮ የሚያቀናው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተመለከተ መግለጫ ተሰጥቷል።

ከ22 አመታት በኋላ ሞሮኮ ላይ በሚኖረው የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፈው እና ከሰሜን አፍሪካ ሀገራት ከሆኑት ግብፅ ሞሮኮ እና ቱኒዚያ ጋር ተደልድሎ ከግንበት 5 ጀምሮ በሚደረገው ውድድር ላይ ለመካፈል ዛሬ ለሊት ወደ ስፍራው የሚያመራውን የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድንን በተመለከተ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የመሰብሰብ አዳራሽ ዛሬ በተሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አሜሪካዊው ቤንጃሚን ዚመር እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አሰሰፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በጣምራ በስፍራው ለተገኙ ጋዜጠኞች መግለጫ መስጠት ችለዋል። በተለይ ከአሰልጣኝ ቅነሳ ጋር በተገናኘ ሙግት መሰል ጭቅጭቅን ጭምር በመግለጫው ያነሱት አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የምንሄደው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች አስደናቂ አቅም ለአለም ለማሳየት ነው። ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ረጅም ጊዜ አብረዋቸው የነበሩ ምክትሎችን የቀነስኩት በራሴ ጥያቄ ነው ፍቅሩ ተፈራ እና ሚካኤል ሚካኤል ወልደሩፋኤል ግን አብረዋቸው ወደ ስፍራ የአሰልጣኝ ቡድን ውስጥ ተካተው እንደሚጓዙ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለው በሴካፋ ይወዳደር ከነበረው ቡድናቸው ላይ አንድ ተጫዋች ብቻ መጨመራቸውን ገልፀው በጥሩ መንገድ ለውድድሩ መዘጋጀታቸውን በቡድኑ ውስጥም ጥሩ አንድነት መኖሩን አክለዋል። በዝግጅት ወቅት የነዳጅ ዕጥረት ከትራንስፖርት አንፃር መስተጓጎል እንደፈጠረ በመግለፅ በመጨረሻም ለአለም ዋንጫው ማለፍ ግባቸው እንደሆነ ጠቁመዋል።

የፌድሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው ሞሮኮ የምንሄደው ከአፍሪካ ዋንጫ ወደ አለም ዋንጫ ለማለፍ ዐላማ አድርገው እንደሆነ ገልፀው በተለይ ለሀገር ውስጥ የሚለፉ ሚዲያዎች እያሉ ከሦስት የመንግስት ተቋማትም ማለትም ፣ ከኢቲቪ ፣ ፋና እና ኦቢኤን ቴሌቪዥን እንዲሁም እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያሉ ጋዜጠኞች እንደሚጓዙ መናገራቸው ቅሬታን ጭምር የፈጠረ ሲሆን ስራ አስፈፃሚው ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኑ ውጤታማ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ እና የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ላደረጉት አስተዋፅኦ አቶ አንበሴ አበበ እና ኢንጅነር ሀይለየሱስ ፍሰሀን በመያዝ ወደ ስፍራው እንደሚያመሩ ጠቁመዋል።

የብሔራዊ ቡድኑ ልዑካን ዛሬ ለሊት 10 ሰዓት ለሐሙስ አጥቢያ ወደ ስፍራው እንደሚያመሩ ተጠቁሟል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...