አማኑኤል ገ/ሚካኤል ወደ ፈረሰኞቹ ምንይሉ ወንድሙ ወደ ጣና ሞገዶቹ አቅንተዋል ምንተስኖት ከበደ /አፍሪካ/ ወደ ኢት.ቡና?

 

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ የመቀለ 70 እንደርታው የጎል ቀበኛ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ፈረሰኞቹን ለመቀላቀል መስማማቱ ታውቋል።በተጨዋቹና ክለቡ መሃል ያለው ድርድር በስኬት በመጠናቀቁ ፌዴሬሽን ሄዶ መፈረም ብቻ እንደቀረው ታውቋል።

በመቀለ 70 እንደርታ ቀሪ የ 1 አመት ውል ያለው ቢሆንም መቀለ 70 የመወዳደሩ ዕድል በመጥበቡ ለቀጣዩ 2 አመት ለፈረሰኞቹ ለመጫወት ሳይስማማ እንዳልቀረ ተነግሯል። በተመሳሳይ በመቀለ 70 እንደርታ የነበረው ምንይሉ ወንድሙም ወደባህር ዳር ከተማ ለማቅናት መስማማቱ ታውቋል።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ተጨዋቹ ለጣና ሞገዶቹ የአንድ አመት ኮንትራት ቢፈልግም ክለቡ 2 አመት ይሁን እያለ ነው። ሁለቱም ወገኖች ድርድራቸውን በስምምነት እያካሂዱ በመሆኑ ድርድሩን ጨርሰው ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ የመቀለ 70 እንደርታው ምንተስኖት ከበደ /አፍሪካ/በኢትዮጲያ ቡና የሙከራ እድል ተሰጥቶት ከቡድኑ ጋር ልምምድ የጀመረ ሲሆን አሰልጣኙ ካሳዬ አራጌ በአቋሙ ከተደሰተ ለቡናማዎቹ ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሶስቱ የትግራይ ክለቦች የማይወዳደሩ ከሆነ ተጨዋቾቹ ወደፈለጉበት ክለብ እንዲገቡ በመፍቀዱ በቀጣዮቹ ቀናት የተጨዋቾች የፊርማ ዜና በብዛት ይሰማል ተብሎ ይጠበቃል።

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport