ኢትዮጵያዊው ኮከብ ለሙከራ ከአንድ ወር በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመራል።

ከመቱ ከተማ ከተገኘ በኋላ በወሎ ኮምቦልቻ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ሰበታ ከተማ እና ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ላለፉት አራት አመታት ደግሞ የኢትዮጵያ መድን ግብ ጠባቂ በመሆን አስደናቂ ብቃቱን ከማሳየቱ ባለፈ ከክለቡ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳው የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያመራ ነው።
ከወራቶች በፊት ኢትዮጵያ ግብፅን በማጣሪያ ጨዋታ ገጥማ አስደናቂ አቋሙን በማሳየቱ በበርካቶች አይን ውስጥ ገብቶ የነበረው ቁመታሙ የግብ ዘብ ያንን መነሻ በማድረግ ከአንድ የደቡብ አፍሪካ ክለብ የሙከራ ዕድል እንደመጣለት ለዝግጅት ክፍላችን ጠቁሟል።
ከአንድ ወር በኋላ በመድን ኮንትራቱ የሚያበቃው ግብ ጠባቂው ከአስረኛ በታች ሆኖ የቋጨው አንድ ክለብ ውስጥ የሙከራ ዕድሉ እንደተመቻቸለትም ሰምተናል።
አስተያየት ይስጡ