ኢትዮጵያዊቷ የካፍ ኢንስትራክተር እና አሰልጣኝ በላይቤሪያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ኮንትራቷን አራዝማለች።

በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ውስጥ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና አዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም ደግሞ የኢትዮጵያ ከ17 ፣ ከ20 አመት በታች እና የሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ጭምር ያሰለጠነችው ራሷን እያሻሻለች የካፍ ኢንስትራክተር እስከመሆን የደረሰችው ኢትዮጵያዊቷ እንስት አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ ላለፉት ሁለት አመታት የላይቤሪያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን እየሰራች የነበረ ሲሆን የሀገሪቷ እግር ኳስ ፌድሬሽን ከማሰልጠን ባለፈ በሀገሪቱ ላሉ አሰልጣኞች በአግባቡ ራሳቸውን እንዲበቁ ከካፍ ጋር በጋራ በመሆን ስልጠናን ስትሰጥ በመቆየቷ ደስተኛ በመሆናቸው ውሏን አራዝመውላታል።
አሰልጣኟ ለቀጣዮቹ ሦስት አመታት እየታየ በሚጨመር አንድ አመት በይፋ ውሏን ማራዘሟን ለሀትሪክ ስፖርት ገልፃለች።
አስተያየት ይስጡ