መነሻ ገጽ መቐለ 70 እንደርታ ጋናዊው ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመድን ፈረመ
መቐለ 70 እንደርታኢትዮጵያ መድህንዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ጋናዊው ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመድን ፈረመ

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ መድን የአጋማሹን አራተኛውን ፈራሚ አግኝቷል።

በአሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ የሚመሩት የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን ከቀናቶች በፊት ከመቐለ 70 እንደርታ በውሰት ተከላካዩን አማኑኤል ልዑልን ፣ ብሩንዲያዊውን የመስመር አጥቂ አልፍሬድ ኑኩሩንዚዛን እና አጥቂው ሳሙኤል ሳሊሶን በአጋማሹ የዝውውር መስኮት ማስፈረማቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዘመን በመቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሎ በተለይ ከቆሙ ኳሶች በግንባር በማስቆጠር የሚታወሰውን የተከላካይ አማካይ እና የተከላካይ ተጫዋቹን ቤንጃሚን ኮቴ ወደ ሀገራችን ተመልሶ ለኢትዮጵያ መድን ፊርማውን አኑሯል።

የ30 አመቱ ይህ ተጫዋች ለሀገሩ ጋና ካሬላ ዩናይትድ እና ህርትስ ኦፍ ኦክ እንዲሁም ለግብፁ ኢስተርን ካምፓኒ እና ለሳውዲ አረቢያው አል ታቃዶም ክለቦች ከተጫወተ በኋላ ወደ ሀገራችን ባለፈው አመት መጥቶ ለመቐለ የተጫወተ ሲሆን ከመቐለ ከተለያየ በኋላ ግን ክለብ አልባ ሆኖ እንደነበር መረጃው ያሳያል ይህም ተጫዋች ዛሬ በይፋ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ መድንን ተቀላቅሎ ወደ ሀዋሳ ማምራቱን አረጋግጠናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...