መቐለ 70 እንደርታ ክለብ የሌለውን አጥቂ ወደ ክለቡ አምጥቷል።
በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የሚመሩት መቐለ 70 እንደርታዎች ከቀናት በፊት አማካዩ ሀብታሙ ንጉሴን የግላቸው ያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ናይጄሪያዊውን 20 አመቱ እንደሆነ የተነገረለትን ፕሪንስ ኦፊሬን የተባለን አጥቂ አስፈርሟል።
ከሀገሩ ክለብ ዲኖ በኋላ ለእስራኤሉ ኤም አታ ቢአሊክ እና ለሳይፕረሱ አክሪታስ ቾሎር ከተጫወተ በኋላ ላለፉት ስድስት ወራት ክለብ ሳይኖረው የተቀመጠውን ይህንን አጥቂ ሞዓም አናብስቱን እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ቀላቅሏል።

አስተያየት ይስጡ