የግብ ዘቡ የመዲናይቱን ክለብ በድጋሚ ሊቀላቀል ነው።
በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከሳምንት በፊት የቀድሞው ግብ ጠባቂያቸውን በረከትን አማረን ለማስፈረም ድርድር ቢያደርጉም በመሐል ግን ዳግም ተፈራን ምርጫቸው አድርገው ልምምድ ከመስራት በዘለለ ሊፈርም ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻም ለቀድሞው ክለቡ ሀዋሳ ከተማ ሊፈርም ችሏል።
ከጋናዊው ግብ ጠባቂ ዳላንድ ኢብራሂም ሌላ ልምድ ያለው ግብ ጠባቂን በስብስባቸው ውስጥ የሌላቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች የቀድሞው የወልዋሎ እና በኢትዮጵያ ቡናም ጥሩ ጊዜ አሳልፎ የነበረውን ግብ ጠባቂው በረከት አማረን ዝውውሩ ቢዘጋም በነፃ የዝውውር መስኮት ሊመልሱት በድጋሚ ማሰባቸውን ባደረኩት ማጣራት ለማወቅ ችያለሁ።
አስተያየት ይስጡ