ከቡናማዎቹ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊ አጥቂ በከፍተኛ የደመወዝ ክፍያ የሀገሩን ክለብ ተቀላቅሏል።
በሀገሩ ዩጋንዳ ለአምስት ክለቦች ተጫውቶ ለምሮኮው ራጃ ካዛብላንካ ለሊቢያዎቹ አል ሂላል እና አል አንዋር በመጫወት በያዝነው አመት መስከረም ወር ላይ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ መጥቶ ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት አመት ውል ተቀላቅሎ ሲጫወት የነበረው ዩጋንዳዊው አጥቂ መሐመድ ሻባን ቀሪ የአንድ አመት ከስድስት ወራት ውል እየቀረው ከሰሞኑ ከቡናማዎቹ ጋር ከተለያየ በኋላ ማረፊያው የሀገሩ ክለብ ኪታራ ሆኗል።
በአሁኑ ሰዓት በዩጋንዳ ፕሪምየር ሊግ አራተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ክለቡ በ240 ሚሊየን የሀገሪቱ ሽልንግ ገንዘብ በሁለት አመት ኮንትራት መቀላቀሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመላክቷል።



